ኢሳይያስ 16:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ደስታና ሐሴትም ከፍሬያማው እርሻ ተወስዶአል፤ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና እልልታ የለም፤ በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ደስታና ሐሤትም ከአትክልቱ ቦታ ተወግዷል፤ በወይን ተክልም ቦታ ዝማሬ የለም፤ እልልታም ቀርቷል። በወይን መጭመቂያ ቦታ የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮችን ሆታ አጥፍቻለሁና። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 እነሆ በፍሬያማው የእርሻ ቦታ አንድ እንኳ ደስተኛ የለም፤ በወይን ተክል ቦታዎች የእልልታና የዝማሬ ድምፅ አይሰማም፤ የወይን ጠጅ ለመጥመቅ የወይን ፍሬ የሚጨምቅ የለም፤ እግዚአብሔር የደስታ እልልታን ሁሉ እንዲቆም አድርጎአል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ደስታና ሐሤትም ከወይን ቦታሽ ተወስዶአል፤ በወይንሽም ቦታዎች ፈጽመው ደስ አይላቸውም፤ በመጥመቂያውም ወይንን አይረግጡም፤ ረጋጮቹን አጥፍቻለሁና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ደስታና ሐሴትም ከፍሬያማው እርሻ ተወስዶአል፥ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና እልልታ የለም፥ በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፥ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |