ኤርምያስ 51:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባቢሎን ኃያላን መዋጋትን ትተዋል በምሽጎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኃይላቸውም ደክሙአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል መቀርቀሪያዎችዋም ተሰብረዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ጦረኞች መዋጋት ትተዋል፤ በምሽጎቻቸው ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኀይላቸው ተሟጥጧል፤ እንደ ሴት ሆነዋል፤ በማደሪያዎቿም እሳት ተለኵሷል፤ የደጇም መወርወሪያ ተሰብሯል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን ወታደሮች ጦርነቱን አቁመው በምሽጋቸው ተቀመጡ፤ የጀግንነትን ወኔ አጥተው እንደ ሴቶች ሆኑ፤ የከተማይቱ የቅጽር በሮች መወርወሪያዎች ተሰባብረዋል፤ ቤቶችም በእሳት ተቃጥለዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋትን ትተዋል፤ በአምባዎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኀይላቸውም ጠፍቶአል፤ እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል፤ መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎን ኃያላን መዋጋትን ትተዋል በአምባዎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፥ ኃይላቸውም ጠፍቶአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል፥ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል። |
እነሆ፥ እንደ እብቅ ይሆናሉ፥ እሳትም ያቃጥላቸዋል ሰውነታቸውንም ከነበልባል ኃይል አያድኑም፤ እርሱም ሰው እንደሚሞቀው ፍም፥ ወይም በፊቱ ሰው እንደሚቀመጥበት እሳት ዓይነት አይደለም።
የጌታ በቀል ነውና በዙሪያዋ ሆናችሁ በእርሷ ላይ ጩኹ፤ እጅዋን ሰጠች፤ ግንቦችዋ ወደቁ ቅጥሮችዋም ፈረሱ፤ እርሷን ተበቀሉ እንደ ሠራችውም ሥሩባት።
አለቆችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ ገዢዎችዋንና ሹማምቶችዋን ኃያላኖችዋንም አሰክራለሁ፥ ለዘለዓለምም አንቀላፍተው አይነቁም፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የተባለው ንጉሥ።
ጤት። በሮችዋ በመሬት ውስጥ ሰጠሙ፥ መወርወሪያዎችዋን አጠፋ፤ ሰበረም፤ ንጉሥዋና አለቆችዋ ሕግ በሌለባቸው በአሕዛብ መካከል አሉ፥ ነቢዮችዋም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አላገኙም።
የደማስቆንም መቀርቀሪያ እሰብራለሁ፥ ነዋሪዎችዋንም ከአዌን ሸለቆ፥ በትረ መንግሥት የያዘውንም ከዔደን ቤት አጠፋለሁ፤ የሶርያም ሕዝብ ተማርከው ወደ ቂር ይሄዳሉ፥” ይላል ጌታ።
ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ውስጥ ፍርድሽ ይፈጸማልና፤” እያሉ ይናገራሉ።