ኢሳይያስ 19:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ፥ የሠራዊት ጌታም በእነርሱ ላይ ከሚያንቀሳቅሳት ከእጁ የተነሣ ይርዳሉ ይፈራሉም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴት ይሆናሉ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ በሚያንቀሳቅሰው ክንዱ ፊት ይፈራሉ፤ ይንቀጠቀጣሉም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 የግብጽ ሕዝብ በፍርሃት እንደ ሴት የሚሆኑበት ጊዜ ይመጣል፤ የሠራዊት አምላክ እነርሱን ለመቅጣት ኀይሉን በሚያሳይበት ጊዜ በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 በዚያም ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከሚያወርድባቸው ፍርሀትና መንቀጥቀጥ የተነሣ ግብፃውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ ከሚያንቀሳቅሳት ከእጁ መንቀሳቀስ የተነሣ ይሸበራሉ ይፈሩማል። ምዕራፉን ተመልከት |