Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ናሆም 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እነሆ፥ በመካከልሽ ያለው ሕዝብሽ ሴቶች ናቸው፤ የምድርሽ በሮች ለጠላቶችሽ በሰፊው ተከፍተዋል፥ መወርወሪያዎችሽን እሳት በልቶአቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እነሆ፤ ጭፍሮችሽ፣ ሁሉም ሴቶች ናቸው! የምድርሽ በሮች፣ ለጠላቶችሽ ወለል ብለው ተከፍተዋል፤ መዝጊያዎቻቸውንም እሳት በልቷቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ወታደሮችሽ ሁሉ እንደ ሴት ፈሪዎች ሆነዋል፤ የጠረፍሽ በሮች ለጠላቶችሽ ክፍት ሆነዋል፤ መወርወሪያዎቹም እሳት በልቶአቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እነሆ፥ በመካከልሽ ያሉ ሕዝብሽ ሴቶች ናቸው፣ የአገርሽ በሮች ለጠላቶችሽ ፈጽሞ ተከፍተዋል፥ እሳትም መወርወሪያዎችህን በልቶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ናሆም 3:13
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የናሱን ደጆች ሰብሮአልና፥ የብረቱንም መወርወሪያ ቈራርጦአልና።


የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችንም በውስጥሽ ባርኮአልና።


በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ፥ የሠራዊት ጌታም በእነርሱ ላይ ከሚያንቀሳቅሳት ከእጁ የተነሣ ይርዳሉ ይፈራሉም።


ሰይፍ በምዋርተኞች ላይ አለ ሞኞችም ይሆናሉ፥ ሰይፍም በኃያላኖችዋ ላይ አለ እነርሱም ይጠፋሉ።


ሰይፍ በፈረሶችዋና በሰረገሎችዋ ላይ በመካከልዋም ባሉት በባዕድ ሕዝብ ሁሉ ላይ አለ፥ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍም በመዝገቦችዋ ላይ አለ እነርሱም ይበዘበዛሉ።


የባቢሎን ኃያላን መዋጋትን ትተዋል በምሽጎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኃይላቸውም ደክሙአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል መቀርቀሪያዎችዋም ተሰብረዋል።


ቴማን ሆይ፥ ሰዎች ሁሉ ከዔሳው ተራራ በግድያ እንዲጠፉ ኃያላን ተዋጊዎችህ ይደነግጣሉ።


መሳፍንቱን ያስባል፤ በአረማመዳቸው ይሰናከላሉ፤ ፈጥነው ወደ ቅጥርዋ ይሮጣሉ፥ መጠለያም ተዘጋጅቷል።


የወንዞቹ በሮች ተከፈቱ፥ ቤተ መንግሥቱም ቀለጠ።


በዚያ እሳት ይበላሻል፥ ሰይፍ ይቆርጥሻል፥ እንደ አንበጣ ይበላሻል። እንደ አንበጣ ብዢ፥ እንደ አንበጣም ተባዢ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች