ኤርምያስ 5:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል፤ እንደ ወፍ አጥማጆችም ያደባሉ፥ ወጥመድንም ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በሕዝቤ መካከል ክፉ ሰዎች አሉና፤ ወፍ እንደሚያጠምዱ ሰዎች፣ ወጥመድ ዘርግተው ሰው እንደሚይዙ ሰዎችም ያደባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሕዝቤ መካከል የሚኖሩ ክፉ ሰዎች አሉ፤ እነርሱም ወፎችን በወጥመድ እንደሚይዝ ሰው ናቸው፤ ስለዚህ ሰዎችን ለማጥመድ መረባቸውን ዘርግተው ያደባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል፤ ሰዎችንም ይዘው ይገድሉ ዘንድ ወጥመድን ይዘረጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል፥ እንደ አጥማጆችም ያደባሉ፥ ወጥመድንም ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ። |
ለነፍሴ ጉድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም ለመናገር ቁጣህንም ከእነርሱ ለመመለስ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስታውስ።
“ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።”
እንዲሁም ደግሞ የስምዖን ወዳጆች የነበሩ የዘብዴዎስ ልጆች ያዕቆብና ዮሐንስም ተደነቁ። ኢየሱስም ስምዖንን፦ “አትፍራ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰዎችን የምታጠምድ ትሆናለህ፤” አለው።