Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 64:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ንጹሕንም በስውር ለመንደፍ ቀስትን ገተሩ፥ ድንገት ይነድፉታል አይፈሩምም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ክፉ ተግባር ለማከናወን እርስ በርስ ይመካከራሉ፤ በስውር ወጥመድ ለመዘርጋት ይነጋገራሉ፤ “ማንስ ሊያየን ይችላል?” ይባባላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ክፉ ሤራ ለማቀነባበር እርስ በርሳቸው ይመካከራሉ፤ ወጥመዳቸውንም የት እንደሚዘረጉ ያቅዳሉ፤ ይህን ሁሉ ሲያደርጉ “ማንም ሊያየን አይችልም” ይላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ቤተ መቅ​ደ​ስህ ቅዱስ ነው በጽ​ድ​ቅም ድንቅ ነው። በም​ድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስ​ፋ​ቸው የሆ​ንህ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንና መድ​ኃ​ኒ​ታ​ችን ሆይ ስማን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 64:5
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔርም ከአባቴ ቤት ባወጣኝ ጊዜ አልኋት፦ ‘በገባንበት አገር ሁሉ ለእኔ የምታደርጊው ወሮታ ይህ ነው፦ ወንድሜ ነው ብለሽ ስለ እኔ ተናገሪ።’”


አንተም፦ “እግዚአብሔር ምን ያውቃል? በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ሊፈርድ ይችላልን?


በልቡም እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔር ረስቶኛል፥ ፈጽሞም እንዳያይ ፊቱን ሰወረ”።


ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች፥ ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን።


አቤቱ፥ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ፥ እርምጃዬንም ሊያሰናክሉ ከመከሩ ከዓመፀኞች አድነኝ።


ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ያላዝኑ፥ በከተማም ይዙሩ።


ጌታ አያይም፥ የያዕቆብ አምላክ አያስተውልም አሉ።


ጠላትም፦ አሳድጄ እይዛቸዋለሁ፥ ምርኮም እካፈላለሁ፥ በእነርሱም ፍላጎቴ ይሞላል፥ ሰይፌንም እመዝዛለሁ፥ እጄም ታጠፋቸዋለች አለ።


ሁሉም እያንዳንዱ ባልንጀራውን ይረዳው ነበር፥ ወንድሙንም፦ “አይዞህ” ይለው ነበር።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱም፦ “ጌታ አያየንም፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ብለዋልና።”


አሁንም ከእኔ ይልቅ እጅግ ኃያል ናቸውና ልወጋቸውና ከምድሪቱ ላሳድዳቸው እችል እንደሆነ፥ ይህን ሕዝብ እባክህ፥ ና ርገምልኝ፤ አንተ የባረከው ቡሩክ የረገምኸውም ርጉም እንደሆነ አውቃለሁና።”


እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ፥ አንድ ሰው የእምነታችሁ ተከታይ ለማድረግ በባሕርና በደረቅ ትዞራላችሁ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ታደርጉታላችሁ።


እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስላሠቃዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ዕጣ ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም ይኖራሉ፤ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ።


ይሁን እንጂ እስራኤላውያን እርስ በርሳቸው ተበረታትተው በመጀመሪያው ቀን ተሰልፈው በነበረበት ስፍራ ላይ እንደገና ቦታ ቦታቸውን ያዙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች