ኤርምያስ 26:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም በላቸው፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ በፊታችሁ በሰጠኋት ሕጌ ለመሄድ እኔን ባትሰሙ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም በላቸው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ባትሰሙኝና የሰጠኋችሁን ሕጌን ባትጠብቁ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ብለህ ተናገር አለኝ፦ “እኔ እግዚአብሔር የሰጠኋችሁን ሕግ ባትከተሉና ባትታዘዙኝ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም በላቸው፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በፊታችሁ በሰጠኋት ሕጌ ትሄዱ ዘንድ ባትሰሙኝ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም በላቸው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በፊታችሁ በሰጠኋት ሕጌ ትሄዱ ዘንድ ባትሰሙኝ፥ |
ነገር ግን የሰንበትን ቀን እንድትቀድሱ፥ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፥ በበሮችዋ ላይ እሳትን አነድዳለሁ፥ የኢየሩሳሌምንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፥ አትጠፋምም።’ ”
እነርሱም ገብተው ወረሱአት፤ ነገር ግን ድምፅህን አልሰሙም በሕግህም አልሄዱም፥ እንዲያደርጉም ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፤ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣህባቸው።
ስላጠናችሁ፥ በጌታም ላይ ኃጢአትን ስለ ሠራችሁ፥ የጌታንም ድምፅ ስላልሰማችሁ፥ በሕጉና በሥርዓቱም በምስክሩም ስላልሄዳችሁ፥ ስለዚህ ዛሬ እንደሆነ ይህ ክፉ ነገር ደርሶባችኋል።”
ወተትና ማር ወደምታፈሰውና ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ባመጣኋቸው ጊዜ ከበሉና ከጠገቡ፥ ከበለጸጉም በኋላ እኔን ንቀው ኪዳኔንም አፍርሰው ወደ ባዕዳን አማልክት ይዞራሉ፤ እነርሱንም ያመልካሉ።
ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።