Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 44:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ስላጠናችሁ፥ በጌታም ላይ ኃጢአትን ስለ ሠራችሁ፥ የጌታንም ድምፅ ስላልሰማችሁ፥ በሕጉና በሥርዓቱም በምስክሩም ስላልሄዳችሁ፥ ስለዚህ ዛሬ እንደሆነ ይህ ክፉ ነገር ደርሶባችኋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ዕጣን በማጠን በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ስለ ሠራችሁና ቃሉን ስላልጠበቃችሁ ሕጉን፣ ሥርዐቱንና ትእዛዙን ስላላከበራችሁ ዛሬ እንደምታዩት ጥፋት መጥቶባችኋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ይህም ሁሉ መቅሠፍት የደረሰባችሁ ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት በማቅረባችሁ፥ እግዚአብሔርን በማሳዘናችሁ፥ ለሕጉ፥ ለድንጋጌውና ለሥርዓቱም ባለመታዘዛችሁ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ስላ​ጠ​ና​ች​ሁት ዕጣን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ላይ ስለ በደ​ላ​ችሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ስላ​ል​ሰ​ማ​ችሁ፥ በሕ​ጉና በሥ​ር​ዐ​ቱም፥ በም​ስ​ክ​ሩም ስላ​ል​ሄ​ዳ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ ዛሬ እንደ ሆነ ይች ክፉ ነገር አግ​ኝ​ታ​ች​ኋ​ለች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ስላጠናችሁ፥ በእግዚአብሔርም ላይ ስለ በደላችሁ፥ የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልሰማችሁ፥ በሕጉና በሥርዓቱም በምስክሩም ስላልሄዳችሁ፥ ስለዚህ ዛሬ እንደ ሆነ ይህች ክፉ ነገር አግኝታችኋለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 44:23
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ራሳቸው የሚሰጡትም መልስ ‘የእስራኤል ሕዝብ የቀድሞ አባቶቻቸውን ከግብጽ ምድር ያወጣ ጌታ አምላካቸውን በመተዋቸው ምክንያት ነው፤ ከዚህም በቀር ለእግዚአብሔር የነበራቸውን ታማኝነት ትተው ሌሎችን አማልክት አመለኩ፤ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ የጥፋት መቅሠፍት ያመጣባቸውም ስለዚህ ነው’ የሚል ነው።”


በዓመፃ የሚያሳድዱኝ ቀረቡ፥ ከሕግህም ራቁ።


አባቶቻችሁ እንደዚህ አድርገው አልነበረምን? አምላካችንስ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ በእኛና በዚህ ከተማ ላይ አምጥቶ አልነበረምን? እናንተም ሰንበትን በማርከሳችሁ በእስራኤል ላይ መዓትን ትጨምራላችሁ አልኋቸው።


የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥ በእነርሱ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።


አይደለም፤ ነገር ግን አሕዛብ የሚሠዉት ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለአጋንንት፤ ከአጋንንት ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አልፈልግም።


ሔት። ኢየሩሳሌም እጅግ ኃጢአት ሠርታለች፥ ስለዚህ ረክሳለች፥ ያከብሩአት የነበሩ ሁሉ ኀፍረተ ሥጋዋን አይተዋታልና አቃለሉአት፥ እርሷም እየጮኸች ታለቅሳለች ወደ ኋላም ዘወር አለች።


“እናንተና አባቶቻችሁ ነገሥታቶቻችሁም አለቆቻችሁም የምድሪቱም ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያጠናችሁትን ዕጣን ጌታ አያስታውሰውምን? በልቡስ አያኖረውምን?


ለሰማይ ንግሥት ማጠንን ለእርሷም የመጠጥን ቁርባን ማፍሰስን ከተውን ወዲህ ግን፥ እኛ ሁሉ ነገር ጐድሎብናል፥ በሰይፍና በራብ አልቀናል።


እናንተም እንድትጠፉ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ እንድትሆኑ፥ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብጽ ምድር ለሌሎች አማልክት አጥናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?


ጌታም አመጣው፥ እንደ ተናገረውም አደረገ፤ በጌታም ላይ ኃጢአት ሠርታችኋልና፥ ድምፁንም አልሰማችሁምና ይህ ነገር በእናንተ ላይ ሆነ።


መድኃኒት ከኀጥኣን ሩቅ ነው፥ ሥርዓትህን አልፈለጉምና።


ነገር ግን ልዑል እግዚአብሔርን ፈተኑት፥ ዐመፁበትም፥ ትእዛዙንም አልጠበቁም፥


እነርሱ ግን የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወርድባቸው ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በጌታ መልክተኞች ይሳለቁ፥ ቃላቱንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።


የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁም፥ በሕጉም ለመመላለስ እንቢ አሉ፥


ሕግህን አልጠበቅሁምና የውኃ ፈሳሽ ከዐይኖቼ ፈሰሰ።


እንዲህም በላቸው፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ በፊታችሁ በሰጠኋት ሕጌ ለመሄድ እኔን ባትሰሙ፥


“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ያመጣሁትን ክፉ ነገር ሁሉ ራሳችሁ አይታችኋል፤ እነሆ፥ ዛሬ ባድማ ሆነዋል፥ የሚቀመጥባቸውም የለም።


ይህም የሆነው ስለ ሠሩት ክፋት እኔን ስላስቈጡኝ፥ በዚህም እናንተም አባቶቻችሁም እነርሱም ለማያውቁአቸው ለሌሎች አማልክት ለማጠንና ለማገልገል ስለ ሄዱ ነው።


እስከ ዛሬ ድረስ አልተዋረዱም አልፈሩምም፥ በእናንተና በአባቶቻችሁም ፊት ባኖርሁት ሕጌና ሥርዓቴ አልሄዱም።


የሰጣቸውንም ድንጋጌ አልተቀበሉም፤ ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ የሰጣቸውንም ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ቸል አሉ፤ ለከንቱ ጣዖቶች በመስገድ ራሳቸውም ከንቱዎች ሆኑ፤ የእነርሱን መጥፎ ምሳሌነት እንዳይወርሱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዝ በመሻር በዙሪያቸው የሚኖሩ የአሕዛብን ልማድ ሁሉ ተከተሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች