ሮቤልም መልሶ፥ “በዚህ ልጅ ላይ፥ ‘ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።
ዘፍጥረት 9:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ እሻዋለሁ፥ ከአራዊት እና ከሰውም ሁሉ እጅ እሻዋለሁ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውን የገደለ ሁሉ ስለ ሟቹ ደም ተጠያቂ ነው፤ የሟቹን ሰው ደም ከገዳዩ፣ ከእንስሳም ይሁን ከሰው እሻለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ በተጠያቂነት ላይ እሻዋለሁ፤ ከእንስሶች ሁሉና ከሰውም ላይ እሻዋለሁ፤ ከሰው ሁሉ የሰውን ሕይወት እሻዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ፤ ከሰውም እጅ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ እሻዋለሁ፥ ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ ከስውም እጅ ከስው ወንድም እጅ፤ የስውን ነፍስ እሻለሁ። |
ሮቤልም መልሶ፥ “በዚህ ልጅ ላይ፥ ‘ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።
ታዲያ በገዛ ቤቱ፥ በገዛ አልጋው ላይ ዐርፎ የተኛውን ንጹሕ ሰው የገደሉትን ክፉ ሰዎች እንዴት የባሰ ቅጣት አይገባቸውም? ደሙን ከእጃችሁ መፈለግ፥ እናንተን ከምድሪቱ ማጥፋት የለብኝምን?”
እንዲሁም ንጉሡ ኢዮአስ ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፥ ልጁንም ዘካርያስን አስገደለው፤ እርሱም ሲሞት፦ “ጌታ ይየው፥ ይበቀለውም” አለ።
በዚህም ምክንያት ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው ጻድቅ ደም ሁሉ በእናንተ ላይ ይደርሳል።
ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፤ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።