ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፥ ዔሳውም በልቡ አለ፦ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል፥ ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
ዘፍጥረት 37:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞቹም፦ “በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ልትገዛ ይሆን?” አሉት። እንደገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ የበለጠ ጠሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞቹም፣ “ለካስ በላያችን ለመንገሥ ታስባለህና! ለመሆኑ አንተ እኛን ልትገዛ!” አሉት፤ ስለ ሕልሙና ስለ ተናገረው ቃል ከፊት ይልቅ ጠሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞቹም “ታዲያ በእኛ ላይ ንጉሥ ሆነህ ልትገዛን ታስባለህን?” ብለው ጠየቁት። ስላየው ሕልምና ስለ ተናገረው ቃል ከበፊቱ ይበልጥ ጠሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቹም፥ “በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ገዢ ትሆነን ይሆን?” አሉት። እንደገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ የበለጠ ጠሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞቹም፦ በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ልትገዛ ይሆን? አሉት። እንደ ገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ ይልቁን ጠሉት። |
ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፥ ዔሳውም በልቡ አለ፦ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል፥ ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
ደግሞም ሌላ ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም፦ “እነሆ ደግሞ ሌላ ሕልምን አለምሁ፥ እነሆ ፀሐይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋክብትም ሲሰግዱልኝ አየሁ።” ሲል ነገራቸው።
ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፥ “ጌታዬ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፤ አንተም የፈርዖን ያህል የተከበርህ ስለሆንህ፥ እባክህን እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ።
የአባትህ በረከቶች ጽኑዓን ከሆኑ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፥ ዘላለማውያን ከሆኑ ከኮረብቶችም በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፥ እነርሱም በዮሴፍ ራስ ላይ ይሆናሉ፥ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነው ራስ አናት ላይ።
እሱም፦ “አንተን በእኛ ላይ አለቃና ዳኛ አድርጎ የሾመህ ማን ነው? ግብፃዊውን እንደ ገደልኸው ልትገድለኝ ትፈልጋለህን?” አለው። ሙሴም፦ “በእውነት ይህ ነገር ታውቆአል” ብሎ ፈራ።
እርሱ ግን ወደ እነርሱ ተመልክቶ “እንግዲህ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥ እርሱ ነው የማዕዘን ራስ የሆነው፤’ ተብሎ የተጻፈው ምን ማለት ነው?
“‘ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው?’ ብለው የካዱትን፥ ይህን ሙሴን በቁጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።
እንግዲህ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ፥ የተቀደሰበትን ያንን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቆጠረ፥ የጸጋውንም መንፈስ ያስቆጣ፥ ቅጣቱ እጅግ የከፋ እንዴት የማይሆን ይመስላችኋል?
አንዳንድ ሥርዓተ አልባዎች ግን፥ “እንዲህ ያለ ሰው እንዴት ሊያድነን ይችላል?” በማለት ናቁት፤ ስጦታም አላመጡለትም። ሳኦል ግን ዝም አለ።
ታላቅ ወንድሙ ኤሊአብ፥ ዳዊት ከሰዎች ጋር ሲነጋገር በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ፥ “ለምን ወደዚህ ወረድህ? እነዚያንስ ጥቂት በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውካቸው? ዕብሪትህንና የልብህን ክፋት ዐውቃለሁ፤ የመጣኸው ጦርነቱን ለማየት ብቻ ነው” አለው።
ሳኦል እጅግ ተቆጣ፤ ይህም ነገር አላስደሰተውም። እርሱም፥ “ለዳዊት ዐሥር ሺህ አሉለት፤ ለእኔ ግን ሺህ ብቻ! እንግዲህ መንግሥት እንጂ ሌላ ምን ቀረው!” አለ።