Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 37:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ እንደሚወደው ባዩ ጊዜ ጠሉት፥ በሰላም ሊያናግሩትም አልቻሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ወንድሞቹም፣ አባታቸው ከእነርሱ አብልጦ የሚወድደው መሆኑን ሲያዩ፣ ዮሴፍን ጠሉት፤ በቅን አንደበትም ሊያናግሩት አልቻሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ወንድሞቹም አባታቸው ከእነርሱ ይልቅ ዮሴፍን እንደሚወድ ባዩ ጊዜ በመቅናት ጠሉት፤ መልካም ቃልም ሊናገሩት አልወደዱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ወን​ድ​ሞ​ቹም አባ​ታ​ቸው ከል​ጆቹ ሁሉ ይልቅ እን​ደ​ሚ​ወ​ድ​ደው በአዩ ጊዜ ጠሉት፤ በሰ​ላም ይና​ገ​ሩ​ትም ዘንድ አል​ቻ​ሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ እንዲወደው ባዩ ጊዜ ጠሉት፥ በሰላም ይናገሩትም ዘንድ አልቻሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 37:4
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፥ ዔሳውም በልቡ አለ፦ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ቀርቦአል፥ ከዚያም በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”


ማንም፦ “እግዚአብሔርን እወደዋለሁ” ቢል ወንድሙን ግን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወድ አይችልምና።


ከክፉው እንደነበረው ወንድሙንም እንደ ገደለው እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለምንስ ገደለው? የእርሱ ሥራ ክፉ፥ የወንድሙ ግን ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።


ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ ይኖራል፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ ጨለማው ዐይኖቹን ስላሳወረው ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።


በጩኸት ደከምሁ ጉሮሮዬም ሰለለ፥ አምላኬን ስጠብቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ።


ታላቅ ወንድሙ ኤሊአብ፥ ዳዊት ከሰዎች ጋር ሲነጋገር በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ፥ “ለምን ወደዚህ ወረድህ? እነዚያንስ ጥቂት በጎች በምድረ በዳ ለማን ተውካቸው? ዕብሪትህንና የልብህን ክፋት ዐውቃለሁ፤ የመጣኸው ጦርነቱን ለማየት ብቻ ነው” አለው።


ዮሴፍም ሕልምን አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥ እነርሱም እንደገና አብዝተው ጠሉት።


ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም። ቃየንም እጅግ ተቈጣ፥ ፊቱም ጠቆረ።


እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባርያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝነት ጊዜያችንን የምናሳልፍ፥ የምንጠላ፥ እርስ በርሳችንም የምንጠላላ ነበርን።


በደሌን እናገራለሁና፥ ስለ ኃጢአቴም እተክዛለሁ።


ቀስተኞች አስቸገሩት፥ ነደፉትም፥ ተቃወሙትም፥


ወንድሞቹም ቀኑበት፥ አባቱ ግን ነገሩን ጠብቆ አኖረው።


የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች በዚህ ይገለጣሉ፤ ጽድቅን የማያደርግ ሁሉ እና ወንድሙን የማይወድ ከእግዚአብሔር አይደለም።


ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር አታልለውሃልና፥ በኋላህም ጮኸዋልና፤ በመልካምም ቢናገሩህም አትመናቸው።”


እንዲሁም አንድ ቤተሰብ እርስ በርሱ ከተለያየ ያ ቤተሰብ ሊቆም አይችልም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች