ዘፍጥረት 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀኑ በመሸ ጊዜ፥ የጌታ እግዚአብሔርን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፥ አዳምና ሚስቱ ከጌታ እግዚእብሔር ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀኑ መሸትሸት ሲል፣ እግዚአብሔር አምላክ በአትክልቱ ስፍራ ሲመላለስ አዳምና ሚስቱ ድምፁን ሰምተው ከእግዚአብሔር አምላክ ፊት በዛፎቹ መካከል ተሸሸጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመሸ ጊዜ፥ እግዚአብሔር አምላክ በአትክልቱ ቦታ ውስጥ ሲመላለስ ድምፁን ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱ እግዚአብሔር አምላክ እንዳያያቸው በዛፎች መካከል ተደበቁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ በገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱም ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱ ከእግዚእብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። |
የእስራኤል ኃጢአት የሆኑት የአዌን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾኽና አሜከላ በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላል፤ እነርሱም ተራሮችን፦ “ሸፍኑን!” ኮረብቶችንም፦ “ውደቁብን!” ይሉአቸዋል።
ዮናስ ግን ከጌታ ፊት ወደ ተርሴስ ለመሸሽ ተነሣ፤ ወደ ያፎም ወረደ፥ ወደ ተርሴስም የምትሄድ መርከብ አገኘ፤ ከጌታ ፊት ሸሽቶ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ለመሄድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርሷ ገባ።
ጌታ እግዚአብሔር ሊያድንህ ጠላቶችህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥ በሰፈርህ መካከል ይሄዳልና ስለዚህ ነውረኛ ነገር እንዳያይብህ፥ ፊቱንም ከአንተ እንዳይመልስ ሰፈርህ የተቀደስ ይሁን።”
የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም፥ ሀብታሞችም፥ ኃይለኞችም፥ አገልጋዮችም፥ ጌቶችም ሁሉ በዋሻዎችና በተራራዎች ዐለቶች ውስጥ ተሰወሩ፤