ዘዳግም 23:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ጌታ እግዚአብሔር ሊያድንህ ጠላቶችህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥ በሰፈርህ መካከል ይሄዳልና ስለዚህ ነውረኛ ነገር እንዳያይብህ፥ ፊቱንም ከአንተ እንዳይመልስ ሰፈርህ የተቀደስ ይሁን።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 አምላክህ እግዚአብሔር ሊጠብቅህ ጠላቶችህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈር ውስጥ ስለሚዘዋወር፣ በመካከልህ አንዳች ነውር አይቶ ከአንተ እንዳይመለስ፣ ሰፈርህ የተቀደሰ ይሁን። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ሰፈራችሁን በሕጉ መሠረት በንጽሕና ጠብቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ ሊጠብቃችሁና በጠላቶቻችሁም ላይ ድልን ሊያጐናጽፋችሁ በሰፈራችሁ ይገኛል፤ እግዚአብሔር ፊቱን ከእናንተ እንዲመልስ የሚያደርገውን አስነዋሪ ነገር ሁሉ አታድርጉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 አምላክህ እግዚአብሔር ሊያድንህ፥ ጠላቶችህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈርህ ውስጥ ይሄዳልና ስለዚህ ነውረኛ ነገር እንዳያይብህ፥ ፊቱንም ከአንተ እንዳይመልስ ሰፈርህ የተቀደሰ ይሁን። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 አምላክህ እግዚአብሔር ሊያድንህ ጠላቶችህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥ በሰፈርህ መካከል ይሄዳልና ስለዚህ ነውረኛ ነገር እንዳያይብህ፥ ፊቱንም ከአንተ እንዳይመልስ ሰፈርህ የተቀደስ ይሁን። ምዕራፉን ተመልከት |