እግዚአብሔርም አለ፦ “በእውነት ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፥ ከእርሱ በኋላ ለዘሩ የዘለዓለም ቃል ኪዳን እንዲሆን ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።
ዘፍጥረት 21:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምንም “ይህችን ባርያ ከነልጇ አባርራት፥ የዚህች ባርያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስምና” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃምንም፣ “ይህችን ባሪያ ከነልጇ አባርራት፤ የዚህች ባሪያ ልጅ፣ ከልጄ ከይሥሐቅ ጋራ አይወርስምና” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሣራም አብርሃምን “ይህችን አገልጋይ ከነልጅዋ ወዲያ አባርልኝ፤ የዚህች አገልጋይ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አብሮ መውረስ አይገባውም” አለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሣራም አብርሃምን አለችው፥ “ይህችን ባሪያ ከነልጅዋ አባርራት፤ የዚህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስምና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርህምንም፤ ይህችን ባሪያ ከነልጅዋ አሳድድ የዚህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስምና አለችው። |
እግዚአብሔርም አለ፦ “በእውነት ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፥ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፥ ከእርሱ በኋላ ለዘሩ የዘለዓለም ቃል ኪዳን እንዲሆን ቃል ኪዳኔን ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።
ነገር ግን የአብርሃም ለነበሩትም ለቁባቶቹ ልጆች አብርሃም ስጦታ ሰጣቸው፥ እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሐቅ ለይቶ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ አገር ሰደዳቸው።
ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ነገር ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ኖሮ ከእኛ ጋር በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ እንዲገለጥ ወጡ።
የገለዓድ ሚስትም ለገለዓድ ወንዶች ልጆች ወለደችለት፤ እነርሱም ባደጉ ጊዜ ዮፍታሔን፥ “ከሌላ ሴት ስለተወለድህ ከቤተሰባችን ምንም ዓይነት ውርስ አይገባህም” በማለት አሳደዱት።