መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና፥ ወደ አሞራውያን፥ ወደ ኬጢያውያን፥ ወደ ፌርዛውያን፥ ወደ ከነዓናውያን፥ ወደ ኤዊያውያንና ወደ እያቡሳውያን ያገባሃል፤ እኔም አጠፋቸዋለሁ።
ዘዳግም 9:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊትህ ዛሬ የሚያልፈው ጌታ እግዚአብሔር መሆኑን እወቅ፥ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊትህም ያዋርዳቸዋል፤ ጌታ ተስፋ እንደሰጠህ አንተም ታሳድዳቸዋለህ፥ በፍጥነትም ታጠፋቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ እንደሚባላ እሳት ከፊትህ ቀድሞ የሚሻገረው አምላክህ እግዚአብሔር መሆኑን ዛሬ ርግጠኛ ሁን፤ እነርሱን ያጠፋቸዋል፤ በፊትህም ድል ያደርጋቸዋል፤ አንተም እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት ታስወጣቸዋለህ፤ በፍጥነትም ትደመስሳቸዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እንደሚባላ እሳት የሆነ እግዚአብሔር አምላክህ በፊትህ የሚሄድ መሆኑን ዛሬ ታያለህ፤ አንተ ወደ ፊት በሄድህ መጠን እርሱ ድል ይነሣቸዋል፤ ስለዚህም እርሱ በሰጠው ተስፋ መሠረት እነርሱን ነቃቅለህ በማባረር በፍጥነት ታጠፋቸዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህም እግዚአብሔር በፊትህ እንዲያልፍ ዛሬ ዕወቅ፤ እርሱ የሚበላ እሳት ነው፤ እርሱ ያጠፋቸዋል፤ በፊትህም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔርም እንደ ነገረህ ከፊትህ ያርቃቸዋል፥ ፈጥኖም ያጠፋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህም እግዚአብሔር እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊትህ እንዲያልፍ ዛሬ እወቅ፤ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊትህም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔርም እንደ ነገረህ አንተ ታሳድዳቸዋለህ፥ ፈጥነህም ታጠፋቸዋለህ። |
መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና፥ ወደ አሞራውያን፥ ወደ ኬጢያውያን፥ ወደ ፌርዛውያን፥ ወደ ከነዓናውያን፥ ወደ ኤዊያውያንና ወደ እያቡሳውያን ያገባሃል፤ እኔም አጠፋቸዋለሁ።
ጌታም ክቡር ድምፁን ያሰማል፥ የክንዱንም መውረድ በሚነድ ቁጣውና በምትበላ እሳት ነበልባል፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በበረዶ፥ ጠጠርም ይገልጣል።
ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የጌታም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።
በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፤ አምላክ የሌላቸው በፍርሃት ራዱ፤ “ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ? ለዘለዓለምም ከምትነድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ መሀል ማን አለ?”
ሰባሪው በፊታቸው ወጥቶአል፤ እነርሱም ሰብረው ወደ በሩ አልፈዋል፥ በእርሱም በኩል ወጡ፤ ንጉሣቸው በፊታቸው ሄዷል፥ ጌታም በራሳቸው ላይ ነው።
“ከግብጽ ያወጣህ አምላክህ ጌታ ከአንተ ጋር ነውና፥ ጠላቶችህን ለመውጋት ወደ ጦርነት ስትሄድ፥ ሠረገሎችንና ፈረሶችን ከአንተ የሚበልጥ ሠራዊትንም በምታይበት ጊዜ አትፍራቸው።
ጌታ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ የሚጥላቸውን ሕዝቦች ሁሉ ታጠፋቸዋለህ፥ ዓይንህም አታዝንላቸውም፤ ወጥመድ ይሆንብሃልና አማልክቶቻቸውን አታምልካቸው።
ጌታ አምላካችሁ እነዚህን ሕዝቦች ጥቂት በጥቂት ከፊትህ ያስወጣቸዋል፤ የዱር አራዊት እንዳይበዙብህ፥ እነርሱን በአንድ ጊዜ ማጥፋት አይቻልህም።
የጌታም ባርያ ሙሴ እንዳዘዘው፥ ኢያሱ የእነዚህን ነገሥታት ከተሞች ሁሉ፥ ነገሥታቶቻቸውንም ሁሉ ያዘ፥ በሰይፍም ስለት መታቸው፥ ፈጽሞም አጠፋቸው።
ጌታም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ መቱአቸውም፥ ወደ ታላቂቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴሮንም፥ በምሥራቅም በኩል ወዳለው ወደ ምጽጳ ሸለቆ አሳደዱአቸው፤ አንድም ሳያስቀሩ መቱአቸው።
አሁን እንግዲህ በዚያን ቀን ጌታ የተናገረውን ይህን ተራራማ አገር ስጠኝ፤ አንተ በዚያ ቀን ዔናቃውያን ታላላቆችና የተመሸጉ ከተሞችም በዚያ እንዳሉ ሰምተህ ነበር፤ ምናልባት ጌታ ከእኔ ጋር ይሆናል፥ ጌታም እንደ ተናገረኝ አሳድዳቸዋለሁ።”
በዚህ ጊዜ ዲቦራ ባራቅን፥ “ተነሣ! ጌታ ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሰጠባት ቀን ይህች ናት፤ እነሆ ጌታ በፊትህ ቀድሞ ወጥቶአል” አለችው። ስለዚህ ባራቅ ዐሥር ሺህ ሰዎችን አስከትሎ ከታቦር ተራራ ወረደ።