ዘዳግም 9:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 እንግዲህ አንተ ልበ ደንዳና ሕዝብ ነህና ጌታ አምላክህ ይህችን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጠህ ስለ ጽድቅህ እንዳልሆነ እወቅ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሔር ይህችን መልካም ምድር እንድትወርሳት የሚሰጥህ ከጽድቅህ የተነሣ አለመሆኑን አስተውል፤ አንተ ዐንገተ ደንዳና ነህና። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እንግዲህ አንተ ልብህ የደነደነ እልኸኛ ስለ ሆንክ እግዚአብሔር ይህችን ለም ምድር የሚሰጥህ አንተ እርስዋን ለመውረስ የተገባህ አለመሆንህን ዕወቅ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 እንግዲህ አንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነህና አምላክህ እግዚአብሔር ይህችን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጠህ ስለ ጽድቅህ እንዳይደለ ዛሬ ዕወቅ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እንግዲህ አንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ነህና አምላክህ እግዚአብሔር ይህችን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጠህ ስለ ጽድቅህ እንዳይደለ እወቅ። ምዕራፉን ተመልከት |