መሳፍንት 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 በዚህ ጊዜ ዲቦራ ባራቅን፥ “ተነሣ! ጌታ ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሰጠባት ቀን ይህች ናት፤ እነሆ ጌታ በፊትህ ቀድሞ ወጥቶአል” አለችው። ስለዚህ ባራቅ ዐሥር ሺህ ሰዎችን አስከትሎ ከታቦር ተራራ ወረደ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 በዚህ ጊዜ ዲቦራ ባርቅን፣ “ተነሣ! እግዚአብሔር ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሰጠባት ቀን ይህች ናት፤ እነሆ እግዚአብሔር በፊትህ ቀድሞ ወጥቷል” አለችው። ስለዚህ ባራቅ ዐሥር ሺሕ ሰዎችን አስከትሎ ከታቦር ተራራ ወረደ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ዲቦራም ባራቅን “እግዚአብሔር አንተን በሲሣራ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ የሚያደርግበት ቀን ዛሬ ስለ ሆነ ተነሥ! እነሆ! እግዚአብሔር ይመራሃል” አለችው፤ ባራቅም ዐሥር ሺህ ወታደሮች ተከትለውት ከታቦር ተራራ ወረደ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ዲቦራም ባርቅን፥ “እግዚአብሔር ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥበት ቀን ዛሬ ነውና ተነሣ፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር በፊትህ ይሄዳል” አለችው። ባርቅም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከትለውት ከታቦር ተራራ ወረደ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ዲቦራም ባርቅን፦ እግዚአብሔር ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሚሰጥበት ቀን ዛሬ ነውና ተነሣ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር በፊትህ ወጥቶአል አለችው። ባርቅም አሥር ሺህ ሰዎች ተከትለውት ከታቦር ተራራ ወረደ። ምዕራፉን ተመልከት |