ዘዳግም 8:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባለጸጋ እንድትሆን ኃይልና ብርታት የሰጠህ ጌታ አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ ይህም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሀብት እንድታፈራ ችሎታ የሰጠህ፣ ለአባቶችህም በመሐላ የገባውን ኪዳን ያጸናልህ እርሱ ስለ ሆነ፣ አምላክህን እግዚአብሔርን ዐስበው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለጸጋ እንድትሆን ኀይልና ብርታት የሰጠህ እግዚአብሔር አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ እርሱ ይህን የሚያደርግበት ምክንያት ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ እርሱ ኀይልን ስለሚሰጥህ አምላክህን እግዚአብሔርን አስበው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ፥ ሀብት ለማከማቸት እርሱ ጉልበት ሰጥቶሃልና አምላክህን እግዚአብሔርን አስብ። |
ባለጠግነትና ክብር ከአንተ ዘንድ ነው፥ አንተም ሁሉን ትገዛለህ፤ ኃይልና ብርታት በእጅህ ነው፤ ታላቅ ማድረግ፥ ለሁሉም ኃይልን መስጠት በእጅህ ነው።
አሜስያስም የእግዚአብሔርን ሰው እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሠራዊት የሰጠሁት መቶ መክሊት ምን ይሆን?” የጌታም ሰው እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ “ጌታ ከዚህ አብልጦ ሊሰጥህ ይችላል።”
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ፍልምያ ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ሀብትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፥ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።
እነሆም፥ ጌታ ሆይ፥ አንተ የሰጠኸኝን የምድሪቱን ፍሬ በኵራት አቅርቤአለሁ።’ አንተም በአምላክህ በጌታ ፊት አኑረው፥ በአምላክህም በጌታ ፊት ስገድ።
ያልሞላሃቸውንም ሀብትን የሞሉ ቤቶች፥ ያልቆፈርካቸውም የተቆፈሩ ጉድጓዶች፥ ያልተከልሃቸውንም የወይን ተክልና የወይራ ዛፎች፥ ስትበላና ስትጠግብ፥
“እንዲህም ይሆናል፥ ይህችን ፍርድ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም፥ ጌታ አምላካችሁ ለአባቶችህ የማለውን ቃል ኪዳንና ዘላለማዊ ፍቅር ለአንተም ይጠብቅልሃል፥
ነገር ግን ጌታ ስለ ወደዳችሁ፥ አባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ አወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ከግብጽ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ አወጣችሁ።
“በሕይወት እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ ጌታም ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱአት፥ ዛሬ እኔ የሰጠኋችሁን ትእዛዝ ሁሉ ለማድረግ ተጠንቀቁ።
ጌታም ጌዴዎንን፦ ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፥ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።