Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 23:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 አባቶቻቸው ስለ በዓል ስሜን እንደ ረሱ፥ እንዲሁ አንዱ ከሌላው ጋር በሚነጋገሩት ሕልሞቻቸው ሕዝቤ ስሜን ለማስረሳት ያስባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 አባቶቻቸው በኣልን በማምለክ ስሜን እንደ ረሱ፣ እነርሱ በሚነጋገሩት ሕልም፣ ሕዝቤ ስሜን እንዲረሳ ያደረጉ ይመስላቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 አባቶቻቸው በዓልን በማምለክ ስሜን እንደ ረሱ እነርሱም ሕልሞቻቸውን እርስ በርሳቸው በመነጋገር ሕዝቤ የእኔን ስም የሚረሳ ይመስላቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 አባ​ቶ​ቻ​ቸው ስለ በዓል ስሜን እንደ ረሱ፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው በሚ​ና​ገ​ራት ሕል​ማ​ቸው ሕዝ​ቤን ስሜን ለማ​ስ​ረ​ሳት ያስ​ባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 አባቶቻቸው ስለ በኣል ስሜን እንደ ረሱ፥ እያንዳንዱ ለባልንጀራው በሚናገራት ሕልማቸው ሕዝቤ ስሜን ለማስረሳት ያስባሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 23:27
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምናሴ አባቱ ሕዝቅያስ ደምስሶአቸው የነበሩትን የአሕዛብ መስገጃ ስፍራዎች እንደገና እንዲሠሩ አደረገ፤ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ባደረገውም ዓይነት በዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ መሠዊያዎችን፥ አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስልን ሠራ፤ የሰማይ ከዋክብትንም አመለከ።


በውኑ ኰረዳ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጣጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን በቍጥር ለማይቆጠሩ ቀናቶች ረስተውኛል።


የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ በመካከላችሁ ያሉት ነብዮቻችሁና ምዋርተኞቻችሁ አያታልሉአችሁ፥ እናንተም የምታልሙትን ሕልም አትስሙ።


ነገር ግን የልባቸውን እልከኝነትና አባቶቻቸው ያስተማሩአቸውን በኣሊምን ተከትለዋልና


ጠንቋዩ ግን ኤልማስ፥ ስሙ እንዲሁ ይተረጐማልና፥ አገረ ገዡን ከማመን ሊያጣምም ፈልጎ ተቃወማቸው።


“ዛሬ እኔ አንተን የማዘውን ትእዛዞቹንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ባለመጠበቅ፥ ጌታ አምላክህን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።


ልብህ እንዳይታበይና፥ ከግብጽም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን፥ ጌታን አምላክህን እንዳትረሳ፤


ባለጸጋ እንድትሆን ኃይልና ብርታት የሰጠህ ጌታ አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ ይህም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።


እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ላይ ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ በኣልንና አስታሮትን እንዲሁም የሶሪያን፥ የሲዶናን፥ የሞዓብን፥ የአሞንንና የፍልስጥኤማውያንን አማልክት አመለኩ፤ እስራኤላውያን ጌታን ስለተዉና ስላላገለገሉት፥


እስራኤላውያን በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ አምላካቸውን ጌታንም ረሱ፤ በኣልንና አስታሮትን አመለኩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች