ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል በፈቃደኝነት ልናቀርብልህ የምንችል እኔ ማን ነኝ? ሕዝቤስ ማን ነው?
ዘዳግም 26:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆም፥ ጌታ ሆይ፥ አንተ የሰጠኸኝን የምድሪቱን ፍሬ በኵራት አቅርቤአለሁ።’ አንተም በአምላክህ በጌታ ፊት አኑረው፥ በአምላክህም በጌታ ፊት ስገድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ እነሆ፤ አንተ የሰጠኸኝን የምድሪቱን በኵራት አምጥቻለሁ።” ቅርጫቱንም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አስቀምጠው፤ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ስገድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እነሆ፥ እኔ እርሱ ከሰጠኝ መጀመሪያ የሆነውን በኲራት አምጥቼአለሁ።’ “ከዚህም ቀጥሎ ቅርጫቱን በእግዚአብሔር ፊት በማኖር ስገድ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እነሆ፥ አቤቱ፥ አንተ የሰጠኸኝን ማርና ወተት የምታፈስሰውን የምድሪቱን ፍሬ ቀዳምያት አቅርቤአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም እነሆ፥ አቤቱ፥ አንተ የሰጠኸኝን የምድሪቱን ፍሬ በኩራት አቅርቤአለሁ። አንተም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አኑረው፥ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ስገድ። |
ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና ከእጅህም የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል በፈቃደኝነት ልናቀርብልህ የምንችል እኔ ማን ነኝ? ሕዝቤስ ማን ነው?
ስለዚህ አንተ የምትፈርድ ሰው ሆይ! የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ ፈራጅ የሆንከው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና።
ጌታ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ሰብል በኲራቱን ሁሉ ውሰድ፤ በቅርጫትም ውስጥ አድርገው፤ ከዚያም ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ጌታ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ሂድ።
ባለጸጋ እንድትሆን ኃይልና ብርታት የሰጠህ ጌታ አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ ይህም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።
እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር፥ ከወንድሞችህም ነቢያት ጋር፥ የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤” አለኝ።