Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 10:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ ወይም ማናቸውንም ነገር ስታደርጉ፥ ሁሉን ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ፣ ወይም ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ፣ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ ወይም ማናቸውንም ነገር ስታደርጉ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ብት​በ​ሉም፥ ብት​ጠ​ጡም የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር አድ​ር​ጉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 10:31
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ የተቀደሱ ይሆናሉ። የሚሠውትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ፥ በእነርሱም ውስጥ ይቀቅሉባቸዋል። በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ ቤት ከእንግዲህ ወዲያ ነጋዴ አይገኝም።


ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፤ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል።


ልቡም ተከፍሎአል። ያላገባች ሴትና ድንግል በሰውነት በመንፈስም እንድትቀደስ የጌታን ነገር ታስባለች፤ ያገባች ግን ባሏን እንዴት ደስ እንደምታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።


እዚያም እናንተ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁ፥ እንዲሁም የራሳቸው ድርሻ ወይም ርስት የሌላቸው በየከተሞቻችሁ የሚኖሩት ሌዋውያን በጌታ በአምላካችሁ ፊት ሐሤት አድርጉ።”


አምላክህ ጌታ በሚመርጠው ስፍራ አንተ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ ወንድና ሴት አገልጋዮችህ፤ በከተሞችህ የሚኖር ሌዋዊም፥ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ትበሉታላችሁ፤ እጅህም በነካው ነገር ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይልሃል።


በዚያም በጌታ በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፤ ጌታ አምላካችሁ እናንተን በባረከበት፥ በምታደርጉት ሁሉ አንተና ቤተሰቦችህ ሐሤት ታደርጋላችሁ።”


በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ፥ በቃል ቢሆን ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።


ሥራችሁንም ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉት እንዲሁ በትጋት ፈጽሙት፤


ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ኃይል ያገልግል፤ በዚህም ዓይነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብራል፤ ክብርና ሥልጣን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች