ሐዋርያት ሥራ 9:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልዳና በሰሮናም የሚኖሩ ሁሉ እርሱን አይተው ወደ ጌታ ተመለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልዳና በሰሮና የሚኖሩትም ሁሉ እርሱን አይተው ወደ ጌታ ተመለሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የልዳና የሳሮናም ነዋሪዎች ሁሉ እርሱን አይተው ወደ ጌታ ተመለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልዳና በሳሮና የሚኖሩም ሁሉ እርሱን አይተው ወደ ጌታችን ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዲያውም ተነሣ። በልዳና በሰሮናም የሚኖሩ ሁሉ እርሱን አይተው ወደ ጌታ ዘወር አሉ። |
እጅግ ያብባል በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር፥ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፤ የጌታንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።
ከቶ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? እንዲህስ ያለ ነገር ማን አይቶአል? በውኑ አገር በአንድ ቀን ታምጣለችን? ወይስ በአንድ ጊዜ ሕዝብ ይወለዳል? ጽዮን እንዳማጠች ወዲያው ልጆችዋን ወልዳለችና።
ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፥ ጌታ አምላካችሁም ቸርና መሐሪ፥ ቁጣው የዘገየ፥ ጽኑ ፍቅሩ የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።