2 ሳሙኤል 22:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድርም ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የሰማያትም መሠረቶች ተናጉ፤ እርሱ ተቆጥቶአልና ራዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የሰማያትም መሠረቶች ተናጉ፤ እርሱ ተቈጥቷልና ተንቀጠቀጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ስለ ተቈጣ ምድር ተናወጠች፤ ተንቀጠቀጠችም፤ የአድማስ መሠረቶች ተናጉ፤ ተነቃነቁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድርም ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የሰማይ መሠረቶችም ተነቃነቁ፤ ተንቀጠቀጡም፤ እግዚአብሔር ተቈጥቶአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድርም ተንቀጠቀጠች፥ ተናወጠችም፥ የሰማዮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ እግዚአብሔርም ተቆጥቶአልና ተንቀጠቀጡ። |
አቤቱ፥ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፥ ከኤዶምያስም ሜዳ በተራመድህ ጊዜ፥ ምድሪቱ ተናወጠች፥ ሰማያቱም አንጠበጠቡ፥ ደመናትም ደግሞ ውኃን አንጠበጠቡ።