Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 22:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር ስለ ተቈጣ ምድር ተናወጠች፤ ተንቀጠቀጠችም፤ የአድማስ መሠረቶች ተናጉ፤ ተነቃነቁም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የሰማያትም መሠረቶች ተናጉ፤ እርሱ ተቈጥቷልና ተንቀጠቀጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ምድርም ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ የሰማያትም መሠረቶች ተናጉ፤ እርሱ ተቆጥቶአልና ራዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ምድ​ርም ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች፤ ተና​ወ​ጠ​ችም፤ የሰ​ማይ መሠ​ረ​ቶ​ችም ተነ​ቃ​ነቁ፤ ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጡም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቈ​ጥ​ቶ​አ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ምድርም ተንቀጠቀጠች፥ ተናወጠችም፥ የሰማዮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ እግዚአብሔርም ተቆጥቶአልና ተንቀጠቀጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 22:8
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መብረቁ በዓለም ላይ ያበራል፤ ምድርም አይታ ትንቀጠቀጣለች።


እርሱ በሚገሥጻቸው ጊዜ፥ የሰማይ አዕማድ በድንጋጤ ይናወጣሉ።


የነጐድጓድህ ጩኸት በዐውሎ ነፋስ አስተጋባ፤ የመብረቅ ብልጭታ ዓለምን አበራ፤ ምድር ተናወጠች፥ ተንቀጠቀጠችም።


እግዚአብሔር ሆይ! ከኤዶም ተራራ በተነሣህ ጊዜ፥ በኤዶምም ምድር ላይ በተራመድህ ጊዜ ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያት ዝናብን አዘነቡ፤ አዎ! ውሃ ከደመናዎች ወደታች ጐረፈ።


እነሆ፥ በድንገት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የጌታ መልአክ ከሰማይ ወርዶ መቃብሩ የተዘጋበትን ድንጋይ አንከባለለና በላዩ ተቀመጠ።


በእግዚአብሔር ፊት ተራራዎች ይንቀጠቀጣሉ፤ ኰረብቶችም ይቀልጣሉ፤ በእግዚአብሔር ፊት ምድር ትናወጣለች፤ ዓለምና በውስጥዋ የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ።


እግዚአብሔር ስለ ተቈጣ ምድር ተናወጠች፤ ተንቀጠቀጠችም፤ የተራሮች መሠረቶች ተናጉ፤ ተነቃነቁም።


ጸሎት ከጨረሱ በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፤ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል ያለ ፍርሀት በድፍረት ተናገሩ።


በዚያን ጊዜ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀዶ ከሁለት ተከፈለ፤ ምድርም ተናወጠች፤ አለቶችም ተሰነጠቁ፤


የሲና አምላክ በመምጣቱ፥ የእስራኤል አምላክ በመገለጡ፥ ምድር ተናወጠች፤ ሰማይም ዝናብን አዘነበ።


እነርሱን ለመዳሰስ የብረት ልብስ ወይም የጦር ዛቢያ ያስፈልጋል፤ በዚያን ጊዜ ባሉበት ፈጽመው ይቃጠላሉ።


መንገድህ በባሕር መካከል ነበር፤ ያለፍከውም በታላላቅ ወንዞች በኩል ነበር፤ ነገር ግን የእግርህ ዱካ አልተገኘም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች