Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 22:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከአፍንጫው የቁጣ ጢስ ወጣ፤ ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ ከእርሱ የሚንበለበል ፍም ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፤ ከአፉ የሚባላ እሳት ነደደ፤ ከውስጡም ፍሙ ጋለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከአፍንጫው የቊጣ ጢስ ወጣ፤ ከአፉም የሚባላ የእሳት ነበልባልና የሚያቃጥል ፍም ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ከቍ​ጣው ጢስ ወጣ፤ ከአ​ፉም የሚ​በላ እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእ​ርሱ ተቃ​ጠለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ከቁጣው ጢስ ወጣ፥ ከአፉም የሚበላ እሳት ነደደ፥ ፍምም ከእርሱ በራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 22:9
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።


ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ መቅሠፍትም ከእግሩ ይወጣል።


የምታቃጥላችሁ እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለችና ከጠላቶችህ ጋር ወደማታውቀው ምድር አሻግርሃለሁስ።”


ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን ቃል ተናግራችኋልና እነሆ፥ በአፍህ ውስጥ ቃሌን እሳት፥ ይህንም ሕዝብ እንጨት አደርጋለሁ፥ ትበላቸዋለችም።


እነሆ፥ የጌታ ስም ከሚነድ ቁጣ፥ ከሚንቦለቦልም ጢስ ጋር ከሩቅ ይመጣል፤ ከንፈሮቹም በቁጣ የተሞሉ ናቸው፥ ምላሱም እንደምትበላ እሳት ናት፤


ፍላጻውን ላከ በተናቸውም፥ መብረቆችን አበዛ አወካቸውም።


ምድርም ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፥ የተራሮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ ተናጉም እግዚአብሔርም ተቈጥቶአልና።


በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፥ በቁጣውም መንፈስ ያልቃሉ።


ከጌታ ተግሣጽ፥ ከአፍንጫው ከሚወጣው፥ ከእስትንፋሱ ቁጣ የተነሣ፥ የባሕር መተላለፊያዎች ታዩ፤ የምድር መሠረቶችም ተገለጡ።


በፊቱ ካለው ብርሃን የእሳት ፍም ነደደ።


እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለች፤ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረትም ታነድዳለች።’”


በተራራው ራስ ላይ የጌታ ክብር ለእስራኤል ልጆች እንደሚባላ እሳት ሆኖ ታያቸው።


ጌታ በእሳት ስለ ወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ ይጤስ ነበር፤ ጢሱም ከእቶን እንደሚወጣ ጢስ ይወጣ ነበር፥ ተራራውም ሁሉ እጅግ ተናወጠ።


ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የጌታም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች