2 ሳሙኤል 22:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባዕዳን ሊለማመጡኝ መጡ፤ እንደ ሰሙኝም በፍጥነት ይታዘዙኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባዕድ አገር ሰዎች ይፈሩኛል፤ እንደ ሰሙኝም ወዲያውኑ ይታዘዙኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባዕዳን ያጐነብሱልኛል፤ ዝናዬን እንደ ሰሙም ይገዙልኛል የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባዕድ ልጆች ዋሹኝ፤ በጆሮ ሰምተው መለሱልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባዕድ ልጆች ደለሉኝ፥ በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ። |
ያገለግሉት ዘንድ የጌታንም ስም ለመውደድ አገልጋዮቹም ለመሆን ወደ ጌታ የሚጠጉትንም መጻተኞች፥ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን፥ በቃል ኪዳኔኔም የሚጸኑትን ሁሉ፥
እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፥ በጌታ የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህም ይገዙልሃል፥ አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።”