Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 56:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ወደ ጌታም የተጠጋ መጻተኛ፦ “በእውነት ጌታ ከሕዝቡ ይለየኛል” አይበል፤ ጃንደረባም፦ “እነሆ፥ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ” አይበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ወደ እግዚአብሔር የተጠጋ መጻተኛ፣ “እግዚአብሔር በርግጥ ከሕዝቡ ይለየኛል” አይበል፤ ጃንደረባም፣ “እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ” አይበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ወደ እግዚአብሔር የተጠጋ ባዕድ ሰው “እግዚአብሔር ከራሱ ሕዝብ ይለየኛል” ብሎ አያስብ፤ ጃንደረባ የሆነ ሰው ልጅ ባለመውለዱ፦ “እንደ ደረቅ ዛፍ ነኝ” አይበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ጠጋ መጻ​ተኛ፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሕ​ዝቡ ይለ​የ​ኛል” አይ​በል፤ ጃን​ደ​ረ​ባም፥ “እነሆ፥ እኔ እንደ ደረቀ ዛፍ ነኝ” አይ​በል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ወደ እግዚአብሔርም የተጠጋ መጻተኛ፦ በእውነት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይለየኛል አይበል፥ ጃንደረባም፦ እነሆ፥ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ አይበል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 56:3
35 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው።


በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።


በእግዚአብሔር ወንጌል እንደ ካህን እያገለገልሁ፥ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ እንድሆን ነው፥ ይህም አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው የተወደደ መሥዋዕት እንዲሆኑ ነው።


ከእነርሱም አንዳንዶቹ ተረድተው ከሚያመልኩም ከግሪክ ሰዎች ብዙ ከከበሩትም ሴቶች ጥቂቶች ያይደሉ፥ ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ።


ጴጥሮስም አፉን ከፍቶ እንዲህ አለ “እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንዳያደላ ነገር ግን በአሕዛብ ሁሉ እርሱን የሚፈራና ጽድቅን የሚያደርግ በእርሱ የተወደደ እንደሆነ በእውነት አስተዋልሁ።


ጌታ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርን አማልክት ሁሉ ያጠፋቸዋልና፤ የሕዝቦችም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች፥ ሁሉም በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


ፊታቸውንም ወደዚያ አቅንተው፦ ኑ፥ ከቶ በማይረሳ በዘለዓለም ቃል ኪዳን ከጌታ ጋር በአንድነት እንሁን፥ ብለው ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ።


በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ሁሉ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘለዓለም ስም እሰጣቸዋለሁ።


ከአንተም ከሚወጡት ከምትወልዳቸው ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦች ይሆናሉ” አለው።


ጌታ ግን ያዕቆብን ይምረዋል፥ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፥ በአገራቸውም ያኖራቸዋል፤ መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፥ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይተሳሰራል።


አንተም ከአንተም ጋር ልጆችህ ለመሠዊያው የሚደረገውን ነገር ሁሉ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የሚሆነውን እንድታደርጉ የክህነታችሁን ግዴታዎች በትጋት ፈጽሙ፥ አገልግሉም፤ ክህነታችሁን እንደ ስጦታ አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁ፤ ሌላም ሰው ቢቀርብ ይገደል።”


ነገር ግን ከእናንተ ጋር በአንድነት ይሁኑ፥ ለድንኳኑም አገልግሎት ሁሉ የመገናኛውን ድንኳን ግዴታዎች ይፈጽሙ፤ ሌላም ሰው ወደ እናንተ አይቅረብ።


የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ጴጥሮስ፥ በጳንጦስ፥ በገላትያ፥ በቀጰዶቅያ፥ በእስያ፥ በቢታንያ፥ ለተበተኑ መጻተኞች፤


ከዚያም ወጥቶ ኢዮስጦስ ወደሚባል እግዚአብሔርን ወደሚያመልክ ሰው ቤት ገባ፤ ቤቱም በምኵራብ አጠገብ ነበረ።


በዚያ ዘመን በዚህም ዓለም ያለ ክርስቶስ ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ፥ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ፥ ተስፋን አጥታችሁና ከእግዚአብሔር ተለይታችሁ እንደ ነበር አስታውሱ።


ወይም ከወገቡ የጐበጠ፥ ወይም ድንክ፥ ወይም የማየት ችግር ያለበት፥ ወይም የእከክ ደዌ ያለበት፥ ወይም ቋቁቻ የወጣበት፥ ወይም የብልቱ ፍሬ የፈረጠ፥ ነውረኛ ሁሉ አይቅረብ።


“ከሕዝብህም ከእስራኤል ያልሆነ እንግዳ ስለ ታላቁ ስምህ ስለ ብርቱውም እጅህ ስለ ተዘረጋውም ክንድህ ከሩቅ አገር በመጣ ጊዜ፥ መጥቶም ወደዚህ ቤት በጸለየ ጊዜ፥


ያገለግሉት ዘንድ የጌታንም ስም ለመውደድ አገልጋዮቹም ለመሆን ወደ ጌታ የሚጠጉትንም መጻተኞች፥ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን፥ በቃል ኪዳኔኔም የሚጸኑትን ሁሉ፥


እንዲሁም በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት መጻተኞች፥ በምድራችሁም ውስጥ ከወለዱአቸው ከእናንተ ጋር ካሉት ከቤተሰቦቻቸው ውስጥ ባርያዎችን ትገዛላችሁ፤ ርስትም ይሆኑላችኋል።


“ጠላቶችህን ልትወጋ በወጣህ ጊዜ ከክፉ ነገር ሁሉ ሰውነትህን ጠብቅ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች