2 ነገሥት 6:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄደን ዛፍ በመቁረጥ የምንኖርበት ቤት በዚያ እንድንሠራ ፍቀድልን!” አሉት። ኤልሳዕም “እሺ መልካም ነው!” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ወደ ዮርዳኖስ ሄደን፣ እያንዳንዳችን ምሰሶ ቈርጠን እናምጣ፣ በዚያም የምንቀመጥበትን መኖሪያ እንሥራ።” እርሱም፣ “ይሁን ሂዱ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄደን ዛፍ በመቊረጥ የምንኖርበት ቤት በዚያ እንድንሠራ ፍቀድልን!” አሉት። ኤልሳዕም “እሺ መልካም ነው!” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ዮርዳኖስም እንሂድ፤ ከእኛም እያንዳንዱ ከዚያ ምሰሶ ያምጣ፥ የምናድርበትም ቤት እንሥራ፥” አሉት፤ እርሱም፥ “ሂዱ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ዮርዳኖስም እንሂድ፤ ከእኛም እያንዳንዱ ከዚያ ምሰሶ ያምጣ፤ የምንቀመጥበትንም ስፍራ በዚያ እንሥራ፤” አሉት፤ እርሱም “ሂዱ” አለ። |
ስምዖን ጴጥሮስ “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” አላቸው። እነርሱም “እኛም ከአንተ ጋር እንመጣለን” አሉት። ወጥተውም ወደ ታንኳይቱ ገቡ፤ ነገር ግን በዚያች ሌሊት ምንም አላጠመዱም።
ወንድሞች ሆይ! ድካማችንንና ጥረታችንን ታስታውሱታላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እየሰበክን በአንዳችሁም ላይ እንኳ ሸክም ላለመሆን ስንል ሌሊትና ቀን እንሠራ ነበር።
ከእናንተ ዘንድ በማንም ላይ ሸክም እንዳንሆንበት ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ የማንንም ሰው እንጀራ እንዲያው በነፃ አልበላንም።