Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 21:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስምዖን ጴጥሮስ “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” አላቸው። እነርሱም “እኛም ከአንተ ጋር እንመጣለን” አሉት። ወጥተውም ወደ ታንኳይቱ ገቡ፤ ነገር ግን በዚያች ሌሊት ምንም አላጠመዱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስምዖን ጴጥሮስም፣ “ዓሣ ላጠምድ መሄዴ ነው” አላቸው፤ እነርሱም፣ “እኛም ከአንተ ጋራ እንሄዳለን” አሉት። ወጥተውም ወደ ጀልባዋ ገቡ፤ በዚያ ሌሊት ግን ምንም አላጠመዱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ስምዖን ጴጥሮስ “ዓሣ ለማጥመድ መሄዴ ነው” አላቸው። እነርሱም “ከአንተ ጋር እንሄዳለን” አሉት፤ ወጥተውም ሄዱና ወደ ጀልባ ገቡ፤ ነገር ግን በዚያች ሌሊት አንድ ዓሣ እንኳ አልያዙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ስም​ዖን ጴጥ​ሮስ፥ “እኔ ዓሣ ላጠ​ምድ እሄ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “እኛም አብ​ረ​ንህ እን​መ​ጣ​ለን” አሉት፤ ሄደ​ውም ወደ ታንኳ ገቡ፤ ግን በዚ​ያች ሌሊት የያ​ዙት ምንም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ስምዖን ጴጥሮስ፦ “ዓሣ ላጠምድ እሄዳለሁ” አላቸው። እነርሱም፦ “እኛም ከአንተ ጋር እንመጣለን” አሉት። ወጥተውም ወደ ታንኳይቱ ገቡ በዚያችም ሌሊት ምንም እላጠመዱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 21:3
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስምዖንም መልሶ፦ “አቤቱ! ሌሊቱን ሙሉ ብንደክምም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ፤” አለው።


ወንድሞች ሆይ! ድካማችንንና ጥረታችንን ታስታውሱታላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እየሰበክን በአንዳችሁም ላይ እንኳ ሸክም ላለመሆን ስንል ሌሊትና ቀን እንሠራ ነበር።


እንግዲህ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ሆነ ወይም የሚያጠጣ ቢሆን ምንም አይደለም።


ወይስ ሥራን ለመተው መብት የሌለን እኔና በርናባስ ብቻ ነን?


እነዚህ እጆቼ በሚያስፈልገኝ ነገር ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት እንዳገለገሉ እናንተ ታውቃላችሁ።


ሥራቸውም አንድ ስለ ነበረ በእነርሱ ዘንድ ተቀምጦ በአንድ ላይ ሠሩ፤ ሥራቸው ድንኳን መስፋት ነበረና።


በነጋም ጊዜ ኢየሱስ በባሕር ዳር ቆመ፤ ደቀመዛሙርቱ ግን ኢየሱስ መሆኑን አላወቁም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች