2 ነገሥት 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም ይህን ሁሉ እያየ “የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች የሆንክ አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ!” እያለ ወደ ኤልያስ ጮኸ፤ ከዚያም በኋላ ኤልያስን ዳግመኛ አላየውም። ኤልሳዕም ከኀዘን ብዛት የተነሣ ልብሱን ከሁለት ቀደደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልሳዕም ይህን አይቶ፣ “አባቴ አባቴ የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች!” ብሎ ጮኸ፤ ዳግመኛም ኤልያስን አላየውም፤ ከዚያም የገዛ ልብሱን ይዞ ከሁለት ቦታ ቀደደው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም ይህን ሁሉ እያየ “የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች የሆንክ አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ!” እያለ ወደ ኤልያስ ጮኸ፤ ከዚያም በኋላ ኤልያስን ዳግመኛ አላየውም። ኤልሳዕም ከሐዘን ብዛት የተነሣ ልብሱን ከሁለት ቀደደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልሳዕም አይቶ፥ “አባቴ! አባቴ ሆይ! የእስራኤል ኀይላቸውና ጽንዓቸው፥” ብሎ ጮኸ። ከዚያም ወዲያ ዳግመኛ አላየውም፤ ልብሱንም ይዞ ከሁለት ቀደደው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልሳዕም አይቶ፥ “አባቴ አባቴ ሆይ! የእስራኤል ሠረገላና ፈረሰኞች!” ብሎ ጮኸ። ከዚያም ወዲያ አላየውም፤ ልብሱንም ይዞ ከሁለት ተረተረው። |
ነቢዩ ኤልሳዕ በብርቱ ደዌ ታሞ ነበር፤ ተኝቶም ሊሞት በሚያጣጥርበት ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ሄዶ፥ ድምፁን ከፍ በማድረግ “አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ! አንተ እኮ የእስራኤል ሕዝብ ኀይላቸውና ጋሻ መከታቸው ነህ!” እያለ አለቀሰለት።
የንዕማንም አሽከሮች ወደ እርሱ ቀረብ ብለው፥ “ጌታችን ሆይ፥ ነቢዩ ሌላ ከባድ ነገር እንድታደርግ ቢያዝህ ኖሮ ትፈጽመው ነበር፤ ታዲያ ነቢዩ ባዘዘህ መሠረት ታጥበህ ከበሽታህ መንጻት ምን ይከብድሃል?” አሉት።
ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደሆንህ፥ ስሙ ማን የልጁስ ስም ማን ነው?
የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ወደ ሕዝቅያስ ላከ፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ ለምነሀልና
ምናልባት በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ አለቃው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራፋስቂስን ቃል አምላክህ ጌታ ሰምቶ እንደሆነ፥ አምላክህ ጌታም ስለ ሰማው ቃል ይገሥጸው እንደሆን፥ ስለዚህ አንተም በሕይወት ስለተረፉት ቅሬታ ጸልይ አሉት።”
መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው፦ “እንግዲህ እስከ ቤተልሔም ድረስ እንሂድ፤ ጌታም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ፤” ተባባሉ።
ሚካም፥ “እንግዲያውስ አብረኸኝ ተቀመጥ፤ አባትም ካህንም ሁነኝ፤ እኔም በዓመት ዐሥር ሰቅል ብር እንዲሁም ልብስና ምግብ እሰጥሃለሁ” አለው።