መሳፍንት 17:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ሚካም፥ “እንግዲያውስ አብረኸኝ ተቀመጥ፤ አባትም ካህንም ሁነኝ፤ እኔም በዓመት ዐሥር ሰቅል ብር እንዲሁም ልብስና ምግብ እሰጥሃለሁ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ሚካም፣ “እንግዲያውስ ዐብረኸኝ ተቀመጥ፤ አባትም ካህንም ሁነኝ፤ እኔም በዓመት ዐሥር ሰቅል ብር እንዲሁም ልብስና ምግብ እሰጥሃለሁ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ሚካም “እንግዲያውስ ከእኔ ጋር ኑር፤ የእኔ አማካሪና ካህን ሁንልኝ፤ በዓመት ዐሥር ብር እንዲሁም ልብስና ምግብ እሰጥሃለሁ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ሚካም፥ “በእኔ ዘንድ ተቀመጥ፤ አባትና ካህንም ሁነኝ፤ እኔም ልብሶችንና ምግብህን፥ በየዓመቱም ዐሥር ብር እሰጥሃለሁ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ሚካም፦ ከእኔ ዘንድ ተቀመጥ፥ አባትና ካህንም ሁነኝ፥ እኔም ልብሶችንና ምግብህን፥ በየዓመቱም አሥር ብር እሰጥሃለሁ አለው። ሌዋዊውም ገባ። ምዕራፉን ተመልከት |