የአሦር ንጉሠ ነገሥት በባቢሎን፥ ኩታ፥ ዓዋ፥ ሐማትና ሰፋርዋይም ተብለው በሚጠሩት ከተሞች ይኖሩ የነበሩትን አሕዛብ አምጥቶ ተሰደው በሄዱት በእስራኤላውያን እግር በመተካት በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፤ እነርሱም እነዚህን ከተሞች ወርሰው በዚያ መኖር ጀመሩ።
2 ነገሥት 19:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመሆኑ የሐማት፥ የአርፋድ፥ የሰፋርዋይም፥ የሄናዕና የዒዋ ከተሞች ነገሥታት የት አሉ?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሐማት ንጉሥ፣ የአርፋድ ንጉሥ፣ የሴፈርዋይም ከተማ ንጉሥ፣ የሄና ንጉሥ ወይም የዒዋ ንጉሥ የት አሉ?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሆኑ የሐማት፥ የአርፋድ፥ የሰፋርዋይም፥ የሄናዕና የዒዋ ከተሞች ነገሥታት የት አሉ?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሐማት ንጉሥ፥ የአርፋድ ንጉሥ፥ የሴፋሩሄም ከተማ ንጉሥ፥ የኤናና የዓዋ ንጉሥ ወዴት አሉ?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሐማት ንጉሥ፥ የአርፋድ ንጉሥ፥ የሴፈርዋይም ከተማ ንጉሥ፥ የሄናና የዒዋ ንጉሥ ወዴት አሉ?” |
የአሦር ንጉሠ ነገሥት በባቢሎን፥ ኩታ፥ ዓዋ፥ ሐማትና ሰፋርዋይም ተብለው በሚጠሩት ከተሞች ይኖሩ የነበሩትን አሕዛብ አምጥቶ ተሰደው በሄዱት በእስራኤላውያን እግር በመተካት በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፤ እነርሱም እነዚህን ከተሞች ወርሰው በዚያ መኖር ጀመሩ።
ታዲያ ይህ ከሆነ የሐማትና የአርፋድ አማልክት የት አሉ? የሰፋርዋይም የሄናዕና የዒዋ አማልክትስ የት ደረሱ? ከእነርሱ አንዱ እንኳ ሰማርያን ከእጄ ማዳን ችሎአልን?
በዚያን ቀን፤ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደገና የተረፈውን የሕዝቡን ትሩፍ ከአሦር፤ ከታችኛው ግብጽ፤ ከላይኛው ግብጽ፤ ከኢትዮጵያ፤ ከኤላም፤ ከባቢሎን፤ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።
የከለዳውያንም ሠራዊት ተከታተላቸው፥ በኢያሪኮም ሜዳ ሴዴቅያስን ደረሱበት፤ እርሱንም ይዘው በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ሪብላ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር አመጡት፤ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ።