1 ሳሙኤል 3:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ዔሊ ሳሙኤልን፥ “ሂድና ተኛ፤ ከእንግዲህ ቢጠራህ ግን፥ ‘ጌታ ሆይ፤ አገልጋይህ ይሰማልና ተናገር’ በል” አለው። ሳሙኤልም ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ዔሊ ሳሙኤልን፣ “ሂድና ተኛ፤ ከእንግዲህ ቢጠራህ ግን፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር’ በል” አለው። ስለዚህም ሳሙኤል ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም “ወደ መኝታህ ተመልሰህ ሂድ፤ እንደገናም የጠራህ እንደ ሆነ ‘ጌታ ሆይ፥ እነሆ እኔ አገልጋይህ እሰማለሁና ተናገር’ በለው” ሲል ሳሙኤልን መከረው። ሳሙኤልም ተመልሶ ወደ መኝታው ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሊም ሳሙኤልን፥ “ልጄ፥ ሄደህ ተኛ፤ ቢጠራህም፦ አቤቱ፥ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር በለው፥” አለው። ሳሙኤልም ሄዶ በስፍራው ተኛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሊም ሳሙኤልን፦ ሄደህ ተኛ፥ ቢጠራህም፦ አቤቱ፥ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር በለው አለው። ሳሙኤልም ሄዶ በስፍራው ተኛ። |
እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ “ጌታ ሆይ! ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?” አለው። ጌታም “ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል፤” አለው።
እርሱም፦ “አይደለሁም፤ እኔ የጌታ ሠራዊት አዣዥ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ” አለ። ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደና፦ “ጌታዬ ለባርያው የሚነግረው ምንድነው?” አለው።
ጌታም ሳሙኤልን ለሦስተኛ ጊዜ ጠራው፤ አሁንም ሳሙኤል ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ፥ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለው። ዔሊም በዚህ ጊዜ ሳሙኤልን ይጠራ የነበረው ጌታ መሆኑን ተረዳ።