Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ዔሊም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ልጄ፥ ሄደህ ተኛ፤ ቢጠ​ራ​ህም፦ አቤቱ፥ ባሪ​ያህ ይሰ​ማ​ልና ተና​ገር በለው፥” አለው። ሳሙ​ኤ​ልም ሄዶ በስ​ፍ​ራው ተኛ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በዚያ ጊዜ ዔሊ ሳሙኤልን፣ “ሂድና ተኛ፤ ከእንግዲህ ቢጠራህ ግን፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር’ በል” አለው። ስለዚህም ሳሙኤል ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ስለዚህም ዔሊ ሳሙኤልን፥ “ሂድና ተኛ፤ ከእንግዲህ ቢጠራህ ግን፥ ‘ጌታ ሆይ፤ አገልጋይህ ይሰማልና ተናገር’ በል” አለው። ሳሙኤልም ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ስለዚህም “ወደ መኝታህ ተመልሰህ ሂድ፤ እንደገናም የጠራህ እንደ ሆነ ‘ጌታ ሆይ፥ እነሆ እኔ አገልጋይህ እሰማለሁና ተናገር’ በለው” ሲል ሳሙኤልን መከረው። ሳሙኤልም ተመልሶ ወደ መኝታው ሄደ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዔሊም ሳሙኤልን፦ ሄደህ ተኛ፥ ቢጠራህም፦ አቤቱ፥ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር በለው አለው። ሳሙኤልም ሄዶ በስፍራው ተኛ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 3:9
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ ከአ​ማ​ል​ክት የሚ​መ​ስ​ልህ የለም፥ እንደ ሥራ​ህም ያለ የለም።


የፈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ ይምጡ፥ አቤቱ፥ በፊ​ት​ህም ይስ​ገዱ፥ ስም​ህ​ንም ያክ​ብሩ፤


ሙሴ​ንም፥ “አንተ ከእኛ ጋር ተና​ገር፤ ነገር ግን እን​ዳ​ን​ሞት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር አይ​ና​ገር” አሉት።


የጌ​ታ​ንም ድምፅ፥ “ማንን እል​ካ​ለሁ? ማንስ ወደ​ዚያ ሕዝብ ይሄ​ድ​ል​ናል?” ሲል ሰማሁ? እኔም፥ “እነ​ሆኝ፥ ጌታዬ፥ እኔን ላከኝ” አልሁ።


እር​ሱም እየ​ፈ​ራና እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ “አቤቱ፥ ምን እን​ዳ​ደ​ርግ ትሻ​ለህ?” አለው፤ ጌታም፥ “ተነ​ሣና ወደ ከተማ ግባ፤ በዚ​ያም ልታ​ደ​ር​ገው የሚ​ገ​ባ​ህን ይነ​ግ​ሩ​ሃል” አለው።


እር​ሱም፥ “እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት አለቃ ነኝ፤ አሁ​ንም ወደ አንተ መጥ​ቼ​አ​ለሁ” አለ። ኢያ​ሱም ወደ ምድር በግ​ም​ባሩ ተደ​ፍቶ ሰገ​ደና፥ “በባ​ሪ​ያህ ዘንድ ምን አቁ​ሞ​ሃል?” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መጥቶ ቆመ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ጠራው። ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ባሪ​ያህ ይሰ​ማ​ልና ተና​ገር” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን እንደ ገና ሦስ​ተኛ ጊዜ ጠራው። እር​ሱም ተነ​ሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነ​ሆኝ ስለ ጠራ​ኸኝ መጣሁ” አለ። ዔሊም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጁን እንደ ጠራው አስ​ተ​ዋለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች