Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 85:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እግዚአብሔር የሚናገረውን እሰማለሁ፥ ወደ እብደታቸው ካልተመለሱ በቀር ጌታ ሰላምን ለሕዝቡና ለቅዱሳኑ ይናገራልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ፣ ማዳኑ ለሚፈሩት በርግጥ ቅርብ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ፥ እርሱን ለሚፈሩት አዳኝነቱ ቅርብ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የፈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ ይምጡ፥ አቤቱ፥ በፊ​ት​ህም ይስ​ገዱ፥ ስም​ህ​ንም ያክ​ብሩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 85:9
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዐይኖቼንም አነሣሁ፥ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ።


ጽድቄን አቀርባለሁ፥ አይርቅም መድኃኒቴም አይዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኃኒትን ለእስራኤል ሰጥቼአለሁ።


ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር እንደሆነ ወይንም እኔ ከራሴ የምናገር እንደሆነ ያውቃል።


ይህም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን፥ ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው።”


“ሩጥ፥ ይህንም ጎልማሳ እንዲህ በለው፦ ኢየሩሳሌም በውስጥዋ ካሉት ሰዎችና እንስሶች ብዛት የተነሣ ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች ትሆናለች።


የጥንት ሕዝብ ወዳሉበት ጉድጓድ ከሚወርዱት ጋር አወርድሻለሁ፥ የሚኖርብሽም እንዳይገኝ ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ቀድሞ በፈረሰችው ስፍራ፥ በታችኛይቱ ምድር አኖርሻለሁ፤ ጌጥሽንም በሕያዋን ምድር አላኖርም።


ምስጋናን የሚሠዋ ያከብረኛል፥ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።


ጳውሎስም ተነሣና በእጁ ጠቅሶ እንዲህ አለ “የእስራኤል ሰዎችና እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሆይ! ስሙ።


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በእኛም ዘንድ አደረ፤ ጸጋንና እውነትን የተመላውን፥ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ ያለውን ክብሩንም አየን።


ከዚያም ጌታ በጽዮን ተራራ ላይና በዚያ በሚሰበሰቡትም ሁሉ ላይ በቀን ደመናንና ጢስን፤ በሌሊትም የሚንበለበለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብሩ ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል፤


መድኃኒት ከኀጥኣን ሩቅ ነው፥ ሥርዓትህን አልፈለጉምና።


ስለዚህም ዔሊ ሳሙኤልን፥ “ሂድና ተኛ፤ ከእንግዲህ ቢጠራህ ግን፥ ‘ጌታ ሆይ፤ አገልጋይህ ይሰማልና ተናገር’ በል” አለው። ሳሙኤልም ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ።


እያንዳንዱም ለባልንጀራው፥ እያንዳንዱም ለወንድሙ እንዲህ ይበልስ፦ ‘ጌታ የመለሰው ምንድነው? ጌታስ ምን ነገር ተናገረ?’


ለነቢዩ እንዲህ ትለዋለህ፦ ‘ጌታ ምን መለሰልህ?’ ‘ጌታስ የተናገረው ምንድነው?’


ለእናንተ የማስበውን አሳብ እኔ ጠንቅቄ አውቃለሁ፥ ይላል ጌታ፤ ለወደፊት የሠመረ ጊዜና ተስፋ ልሰጣችሁ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ የምነግርህን ቃሌን ሁሉ በልብህ ያዝ፥ በጆሮህም ስማ።


በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፤ ምን እንደሚለኝና በአቤቱታዬም ምን መልስ እንደምሰጥ ለማየት እጠባበቃለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች