1 ነገሥት 5:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አባቴ ዳዊት በዙሪያው ከነበሩት የጠላት አገሮች ሠራዊት ጋር ሲዋጋ መኖሩን አንተ ራስህ ታውቀዋለህ፤ በጠላቶቹ ላይ ጌታ ድልን እስኪያጐናጽፈው ድረስ ለእግዚአብሔር ለጌታው ቤተ መቅደስ ለመሥራት አለመቻሉንም ታስታውሳለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አባቴ ዳዊት በዙሪያው ሁሉ ከገጠመው ጦርነት የተነሣ፣ እግዚአብሔር ጠላቶቹን ከእግሩ በታች እስኪጥልለት ድረስ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስ መሥራት እንዳልቻለ ታውቃለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አባቴ ዳዊት በዙሪያው ከነበሩት የጠላት አገሮች ሠራዊት ጋር ሲዋጋ መኖሩን አንተ ራስህ ታውቀዋለህ፤ በጠላቶቹ ላይ ድልን እስኪያጐናጽፈው ድረስ ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ለመሥራት አለመቻሉንም ታስታውሳለህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔር ከእግሩ በታች እስኪጥልለት ድረስ በዙሪያው ስለ ነበረ ጦርነት አባቴ ዳዊት ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ስም ቤት መሥራት እንዳልቻለ አንተ ታውቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “እግዚአብሔር ከእግሩ በታች እስኪጥልለት ድረስ በዙሪያው ስለ ነበረ ሰልፍ አባቴ ዳዊት የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት እንዳልቻለ አንተ ታውቃለህ። |
ነገር ግን የጌታ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ ‘እጅግ ደም አፍስሰሃል፥ ታላቅም ውግያ አድርገሃል፤ በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም።
ንጉሡም ዳዊት ተነሥቶ በመቆም እንዲህ አለ፦ “ወንድሞቼና ሕዝቤ ሆይ! ስሙኝ፤ ለጌታ ለቃል ኪዳኑ ታቦትና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የሚሆን የማረፍያ ቤት ለመሥራት እኔ በልቤ አስቤያለሁ፤ ለግንባታም የሚያስፈልገውን አዘጋጅቻለሁ፤
የማዕዱንም መብል፥ የሹማምንቱንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም አሠራር አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም አለባበሳቸውንም፥ በጌታም ቤት የሚያሳርገውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ እጅግ ተደነቀች።
ለአንድ ቀን ይሠራ የነበረው አንድ በሬ፥ ስድስት የተመረጡ በጎች ነበር፤ ዶሮዎችም ይዘጋጁልኝ ነበር፥ በየዐሥር ቀኑም ብዛት ያለው ልዩ ልዩ ዓይነት ወይን ጠጅ ይዘጋጅልኝ ነበር፤ ይህም ሆኖ ግን የንጉሡን ምግብ አልሻም ነበር በዚህ ሕዝብ ላይ ሥራው ከብዶ ነበርና።
እነዚያንም ነገሥታት ወደ ኢያሱ ባወጡአቸው ጊዜ ኢያሱ የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፥ ከእርሱም ጋር የሄዱትን የተዋጊዎቹን የጦር አዛዦች እንዲህ አላቸው፦ “ቅረቡ፥ በእነዚህም ነገሥታት አንገት ላይ እግራችሁን አኑሩ።” ቀረቡም በአንገታቸውም ላይ እግራቸውን አኖሩ።