Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 5:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በዙሪያችን ካሉት፥ ወደ እኛ ከመጡት አሕዛብ ሌላ ከአይሁድና ከሹማምቱ መቶ አምሳ ሰዎች በገበታዬ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከዚህም በላይ በዙሪያችን ካሉት፣ ወደ እኛ ከሚመጡት አሕዛብ ሌላ አንድ መቶ ዐምሳ አይሁድና ሹማምት ከማእዴ ይካፈሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከአካባቢ አገሮች ወደ እኔ ከመጡት ሕዝቦች ሌላ በየዕለቱ ከእኔ ጋር የሚመገቡ አይሁድና የመሪዎቻቸው ቊጥር አንድ መቶ ኀምሳ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ደግ​ሞም በዙ​ሪ​ያ​ችን ካሉት አሕ​ዛብ ወደ እኛ ከመ​ጡት ሌላ ከአ​ይ​ሁ​ድና ከሹ​ሞቹ መቶ አምሳ ሰዎች በገ​በ​ታዬ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ደግሞም በዙሪያችን ካሉት አሕዛብ ወደ እኛ ከመጡት ሌላ ከአይሁድና ከሹማምቱ መቶ አምሳ ሰዎች በገበታዬ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 5:17
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይልቅስ አሁን እስራኤላውያንን ሁሉ እንዳገኛቸው በቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብልኝ፤ በንግሥት ኤልዛቤል ማእድ የሚቀለቡትን አራት መቶ ኀምሳ የባዓል ነቢያትንና አራት መቶ የአሼራ ነቢያትን ጭምር ይዘህ ና።”


ዳዊትም፥ “አትፍራ፤ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል ቸርነት አደርግልሃለሁ። የአባትህን የሳኦልን ምድር በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም ከማዕዴ ትበላለህ” አለው።


ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ተቀበሉ።


ከበርቴ ሰው ግን ለመከበር ያስባል፤ ለመከበርም ጸንቶ ይኖራል።


መፊቦሼትም ሁልጊዜ ከንጉሥ ማእድ ስለሚበላ ይኖር የነበረው በኢየሩሳሌም ነው፤ ሁለት እግሮቹም ሽባ ነበሩ።


በተጨማሪም ለዚህ የቅጥር ሥራ እራሴን ሰጠሁ፥ እርሻም አልገዛንም፤ አገልጋዮቼም ሁሉ ወደዚያው ወደ ሥራው ተሰበሰቡ።


“አባቴ ዳዊት በዙሪያው ከነበሩት የጠላት አገሮች ሠራዊት ጋር ሲዋጋ መኖሩን አንተ ራስህ ታውቀዋለህ፤ በጠላቶቹ ላይ ጌታ ድልን እስኪያጐናጽፈው ድረስ ለእግዚአብሔር ለጌታው ቤተ መቅደስ ለመሥራት አለመቻሉንም ታስታውሳለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች