Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ዜና መዋዕል 22:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ነገር ግን የጌታ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ ‘እጅግ ደም አፍስሰሃል፥ ታላቅም ውግያ አድርገሃል፤ በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ነገር ግን ከእግዚአብሔር እንዲህ የሚል ቃል መጣልኝ፤ ‘አንተ ብዙ ደም አፍስሰሃል፤ ብዙ ጦርነትም አድርገሃል፤ በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም ያፈሰስህ ስለ ሆነ፣ አንተ ለስሜ ቤት አትሠራልኝም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር ግን ‘አንተ ብዙ ሰው ገድለሃል፤ በብዙ ጦርነቶችም ላይ ውጊያ አድርገሃል፤ ብዙ ደም በማፍሰስህም ቤተ መቅደስ እንድትሠራ አልፈቅድልህም’ ብሎኛል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እን​ዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ እጅግ ብዙ ደም አፍ​ስ​ሰ​ሃል፤ ታላ​ቅም ሰልፍ አድ​ር​ገ​ሃል፤ በፊ​ቴም በም​ድር ላይ ብዙ ደም አፍ​ስ​ሰ​ሃ​ልና ለስሜ ቤት አት​ሠ​ራም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ ‘እጅግ ደም አፍስሰሃል፤ ታላቅም ሰልፍ አድርገሃል፤ በፊቴ በምድር ላይ ብዙ ደም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዜና መዋዕል 22:8
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር ግን፦ ‘የጦር አርበኛ ነህና፥ ደምም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም’ ብሎኛል።


“አባቴ ዳዊት በዙሪያው ከነበሩት የጠላት አገሮች ሠራዊት ጋር ሲዋጋ መኖሩን አንተ ራስህ ታውቀዋለህ፤ በጠላቶቹ ላይ ጌታ ድልን እስኪያጐናጽፈው ድረስ ለእግዚአብሔር ለጌታው ቤተ መቅደስ ለመሥራት አለመቻሉንም ታስታውሳለህ።


በሰባተኛውም ቀን ልብሳችሁን ታጥባላችሁ፥ ንጹሕም ትሆናላችሁ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈሩ ትገባላችሁ።”


ልብስንም፥ ከቁርበትም የተዘጋጀውን ሁሉ፥ ከፍየልም ጠጉር ከእንጨትም የተሠራውን ሁሉ አንጹ።”


ነገር ግን ለስሜ ቤት የሚሠራው ከአንተ የሚወለደው ልጅ እንጂ አንተ አይደለህም’።


አሁንም፥ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ከአንተ በኋላ በጌታዬ በንጉሥ ዙፋን ላይ የሚቀመጠውን ትነግራቸው ዘንድ የእስራኤል ሁሉ ዐይን ይመለከትሃል።


በዚህ ዓይነት ሠራተኞቹ በንጉሥ ሰሎሞን ትእዛዝ ለቤተ መቅደሱ መሠረት የሚሆኑ ታላላቅ ድንጋዮችን ፈለጡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች