Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 10:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እነዚያንም ነገሥታት ወደ ኢያሱ ባወጡአቸው ጊዜ ኢያሱ የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፥ ከእርሱም ጋር የሄዱትን የተዋጊዎቹን የጦር አዛዦች እንዲህ አላቸው፦ “ቅረቡ፥ በእነዚህም ነገሥታት አንገት ላይ እግራችሁን አኑሩ።” ቀረቡም በአንገታቸውም ላይ እግራቸውን አኖሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እነዚህን ነገሥታት ባመጡለትም ጊዜ፣ ኢያሱ መላውን የእስራኤልን ወንዶች ከጠራ በኋላ ዐብረውት የመጡትን የጦር አዛዦች፣ “ወደዚህ ቅረቡና እግሮቻችሁን በእነዚህ ነገሥታት ዐንገት ላይ አድርጉ” አላቸው፤ እነርሱም ወደ ፊት ቀርበው እግራቸውን በነገሥታቱ ዐንገት ላይ አሳረፉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ወደ ኢያሱም አመጡአቸው፤ ኢያሱም የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ጠራ፤ ከእርሱ ጋር የዘመቱት የጦር መኰንኖችም መጥተው እግራቸውን በነገሥታቱ አንገት ላይ እንዲያደርጉ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም እንደ ታዘዙት አደረጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እነ​ዚ​ያ​ንም ነገ​ሥት ወደ ኢያሱ ባመ​ጡ​አ​ቸው ጊዜ ኢያሱ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የሄ​ዱ​ትን የተ​ዋ​ጊ​ዎ​ችን አለ​ቆች “ቅረቡ፤ በእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሥት አን​ገት ላይ እግ​ራ​ች​ሁን አኑሩ” አላ​ቸው። ቀረ​ቡም በአ​ን​ገ​ታ​ቸ​ውም ላይ እግ​ራ​ቸ​ውን አኖሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እነዚያንም ነገሥታት ወደ ኢያሱ ባወጡአቸው ጊዜ ኢያሱ የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፥ ከእርሱም ጋር የሄዱትን የሰልፈኞች አለቆች፦ ቅረቡ፥ በእነዚህም ነገሥታት አንገት ላይ እግራችሁን አኑሩ አላቸው። ቀረቡም በአንገታቸውም ላይ እግራቸውን አኖሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 10:24
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈጽሜ አጠፋኋቸው፤ አስጨነቅኻቸው ተመልሰውም እንዳይቆሙ፥ ከእግሬም ሥር ወድቀዋል።


የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው።


በመኰንኖችም ላይ ውርደትን ዘረገፈ፥ መንገድም በሌለበት በምድረ በዳ አንከራተታቸው።


የዳዊት መዝሙር። ጌታ ጌታዬን፦ “ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።”


ጌታ በቀኝህ፥ ነገሥታትን በቁጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል።


ለጦርነት ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፥ በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ።


በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፥ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።


ነፍስሽንም፦ “በአንቺ ላይ እንድንረማመድ ዝቅ በዪ” በሚሉአት በአስጨናቂዎችሽ እጅ አኖረዋለሁ፤ ጀርባሽንም ለሚሻገሩት እንደ መሬትና እንደ መንገድ አደረግሽላቸው።


እኔ በምሠራበት ቀን ክፉዎችን ትረግጧቸዋላችሁ፥ ከእግራችሁ ጫማ በታች አመድ ይሆናሉና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


የሰላም አምላክ ሰይጣንን ከእግራችሁ ሥር ፈጥኖ ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።


እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፥ በጌታ የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህም ይገዙልሃል፥ አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።”


ነገር ግን ከመላእክት፥ “ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፤” ከቶ ለማን ብሎአል?


ከዚያም የበኲር ልጁ ወደ ሆነው ዮቴር ዘወር ብሎ፥ “ግደላቸው” አለው፤ ዮቴር ግን ትንሽ ልጅ ነበርና ስለ ፈራ ሰይፉን አልመዘዘም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች