መጽሐፈ ጦቢት 14:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ፥ ወደ ሜዶን ሂድ፤ ትጠፋ ዘንድ እንዳላት ነቢዩ ዮናስ በነነዌ የተናገረውን ነገር ሁሉ አውቃለሁና፤ በሜዶን ግን እስከ ዘመኑ ድረስ ሰላም ይሆናል። ወንድሞቻችንም ከተባረከች ምድር ሁሉ ወደየሀገሩ ይበተኑ ዘንድ አላቸው፤ ኢየሩሳሌምም ምድረ በዳ ትሆናለች፤ በእርስዋም ያለ የእግዚአብሔር ቤት ይቃጠላል፤ እስከ ዘመኑም ድረስ ምድረ በዳ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ልጄ ሆይ ልጆችህን ይዘህ በፍጥነት ወደ ሜዶን ሂድ፤ ምክንያቱም ነቢዩ ናሆም በነነዌ ላይ የተናረገውን የእግዚአብሔርን ቃል አምናለሁና፤ ሁሉ ነገር ይፈጸማል፤ የእግዚአብሔር ልዑካን፥ የእስራኤል ነብያት በአሦርና በነነዌ ላይ የተነበዩት ሁሉ ይፈጸማል። ከተናገሩት ቃል ሁሉ አንድም ነገር አይጐድልም፤ ሁሉም ነገር በጊዜው ይፈጸማል። ከአሦርና ከባቢሎን አገር ይልቅ በሜዶን አገር ከአደጋ ማምለጥ ይቻላል፥ ምክንያቱም እግዚአብሔር የተናረገው ሁሉ እንደሚሆንና እንደሚፈጸም አውቃለሁ፤ ይሆናልም። ከትንቢት አንድ ቃል እንኳ ሳይፈጸም የሚቀር የለም። በእስራኤል የሚኖሩ ወንድሞቻችን ከተቆጠሩ በኋለ ከውድ ሀገራቸው ይሰደዳሉ። የእስራኤል ድንበሮች በሙሉ በረሃ ይሆናሉ፤ ሰማርያና ኢየሩሳሌምም በረሃ ይሆናሉ፤ የእግዚአብሔር ቤትም ተቃጥሎ ለጥቂት ጊዜ ይፈራርሳል። |