ሞት ሆይ፥ ኀይል በሌለው፥ ፈጽሞም ባረጀ፥ ሊያደርገውም የሚችል ምንም በሌለው፥ የሚያውቀውም በሌለው፥ በድሃ ሰው ላይ በምትመጣ ጊዜ ፍርድህ እንዴት መልካም ነው!
ሞት ሆይ! ኃይሉ ለደከመበትና ችግር ላጐሳቆለው፥ እርጅና ለተጫነውና የሺህ ጭንቀቶች ጐሬ ለሆነው፥ ለቁጡውና ትዕግሥት ላጣው ፍርድህ አስደሳች ነው።