አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኀይል፥ ክብርም፥ ድልና ጽንዕ የአንተ ነው፤ ነገሥታቱና ሕዝቡ ሁሉ በፊትህ ይደነግጣሉ።
መዝሙር 148:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ስም ያመሰግናሉ። ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ በሰማይና በምድር ያመሰግኑታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስሙ ብቻውን ከፍ ያለ ነውና፣ ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ነውና፣ እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታን ስም ያመስግኑ፥ ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏልና፥ ክብሩም በሰማይና በምድር ላይ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእርሱ ስም ከሌሎች ስሞች ስለሚበልጥና ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ከፍ ያለ ስለ ሆነ ሁሉም የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ! |
አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኀይል፥ ክብርም፥ ድልና ጽንዕ የአንተ ነው፤ ነገሥታቱና ሕዝቡ ሁሉ በፊትህ ይደነግጣሉ።
ጕሮሮው እጅግ ጣፋጭ ነው፥ ሁለንተናውም የተወደደ ነው፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ልጅ ወንድሜ ይህ ነው፥ ወዳጄም ይህ ነው።
አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከወንድሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወንድምሽ ማን ነው? ይህን ያህል መሐላ አምለሽናልና ከወንድሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወንድምሽ ማን ነው?
በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፥ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ክብሩን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ አስታውሱ።
አንዱም ለአንዱ፥ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች” እያለ ይጮኽ ነበር።
ክርስቶስን አገለግለው ዘንድ፥ ሁሉን የተውሁለት፥ እንደ ጕድፍም ያደረግሁለት የጌታዬን የኢየሱስ ክርስቶስን ኀይልና ገናናነት ስለማውቅ ሁሉን እንደ ኢምንት ቈጠርሁት።