ዕረፍትም መልካም መሆንዋን፥ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን በአየ ጊዜ ምድርን ያርሳት ዘንድ ትከሻውን ዝቅ አደረገ፤ በሥራም ገበሬ ሆነ።
ኢያሱ 17:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች በረቱባቸው፤ ከነዓናውያንንም ገዙአቸው፤ ነገር ግን ፈጽመው አላጠፉአቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን በበረቱ ጊዜ ግን ከነዓናውያንን የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው እንጂ ከዚያ ፈጽመው አላባረሯቸውም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች በጸኑ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አደረጉአቸው፥ ፈጽመውም አላሳደዱአቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን በኀይል እየበረቱ ቢሄዱም እንኳ ከነዓናውያንን ሁሉ አላባረሩአቸውም፤ ነገር ግን የጒልበት ሥራ እንዲሠሩላቸው ያስገድዱአቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች በጸኑ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ግብር አስገበሩአቸው፥ ፈጽመውም አላሳደዱአቸውም። |
ዕረፍትም መልካም መሆንዋን፥ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን በአየ ጊዜ ምድርን ያርሳት ዘንድ ትከሻውን ዝቅ አደረገ፤ በሥራም ገበሬ ሆነ።
በሳኦል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ለብዙ ጊዜ ጦርነት ሆነ፤ የዳዊት ቤት እየበረታ፥ የሳኦል ቤት ግን እየደከመ የሚሄድ ሆነ።
የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ ያልቻሉትን፥ ልጆቻቸውን ሰሎሞን እሰከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው።
በጋዜርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን ኤፍሬም አላጠፋቸውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ ገባርም ሆኑ።
ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
ዛብሎንም በቄድሮንና በአማን የሚኖሩትን ሰዎች አላጠፋቸውም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በመካከላቸው ተቀመጡ፤ ግብርም የሚገብሩላቸው ሆኑ።
ንፍታሌምም የቤትሳሚስንና የቤቴኔስን ሰዎች አላጠፋቸውም፤ በምድሩም በተቀመጡት በከነዓናውያን መካከል ተቀመጡ፤ ነገር ግን በቤትሳሚስና በቤቴኔስ የሚኖሩ ሰዎች ገባሮች ሁኑላቸው።
አሞሬዎናውያንም ድብና ቀበሮዎች በሚኖሩበት በመርስኖኖስ ተራራ መቀመጥ ጀመሩ፤ ነገር ግን የዮሴፍ ወገን እጅ በአሞሬዎናውያን ላይ ጸናች፤ ገባርም አደረጉአቸው።