Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 17:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እስራኤላውያን በበረቱ ጊዜ ግን ከነዓናውያንን የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው እንጂ ከዚያ ፈጽመው አላባረሯቸውም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የእስራኤልም ልጆች በጸኑ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ አደረጉአቸው፥ ፈጽመውም አላሳደዱአቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እስራኤላውያን በኀይል እየበረቱ ቢሄዱም እንኳ ከነዓናውያንን ሁሉ አላባረሩአቸውም፤ ነገር ግን የጒልበት ሥራ እንዲሠሩላቸው ያስገድዱአቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በረ​ቱ​ባ​ቸው፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ገዙ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ፈጽ​መው አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የእስራኤልም ልጆች በጸኑ ጊዜ ከነዓናውያንን የጉልበት ግብር አስገበሩአቸው፥ ፈጽመውም አላሳደዱአቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 17:13
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህ ሁሉ ሆኖ የኤፍሬም ዘሮች በጌዝር የሚኖሩትን ከነዓናውያን ከዚያ አላባረሯቸውም ነበር፤ ከነዓናውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከኤፍሬም ዘሮች ጋራ ዐብረው ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ ይገደዳሉ።


ኀይልን በሚሰጠኝ በርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ።


ነገር ግን በጌታችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ዕውቀት እደጉ። ለርሱ አሁንም፣ ለዘላለምም ክብር ይሁን! አሜን።


በተረፈ በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ ጠንክሩ።


በዳዊት ቤትና በሳኦል ቤት መካከል የነበረው ጦርነት ብዙ ጊዜ ቈየ፤ ዳዊት እየበረታ ሲሄድ፣ የሳኦል ቤት ግን እየተዳከመ መጣ።


አሞራውያንም በሔሬስ ተራራ፣ በኤሎንና በሻዓልቢም ኑሯቸውን ቀጠሉ፤ ይሁን እንጂ የዮሴፍ ወገን በበረታ ጊዜ ተገድደው የጕልበት ሥራ ከመሥራት አላመለጡም።


ንፍታሌምም በቤትሳሚስና በቤትዓናት የሚኖሩትን አላስወጣም፤ ስለዚህ የንፍታሌም ነገድ በምድሪቱ ከሚኖሩት ከነዓናውያን ጋራ ዐብረው ኖሩ፤ ይሁን እንጂ በቤትሳሚስና በቤትዓናት የሚኖሩት ለእነርሱ የጕልበት ሥራ ተገድደው ይሠሩ ነበር።


ዛብሎንም እንደዚሁ በቂድሮንና በነህሎል የነበሩትን በመካከላቸው የቀሩትን ከነዓናውያንን አላስወጣም፤ ነገር ግን የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዳቸው።


እስራኤላውያን በበረቱ ጊዜ ግን ከነዓናውያንን የጕልበት ሥራ እንዲሠሩ አስገደዷቸው እንጂ ፈጽሞ አላስወጧቸውም።


ማረፊያ ቦታው መልካም፣ ምድሪቱም አስደሳች መሆኗን ሲያይ፣ ትከሻውን ለሸክም ያመቻቻል፤ ተገድዶም ያገለግላል።


እስራኤላውያን ዘሮቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት ያልቻሉትንና በምድሪቱ የቀሩትን የእነዚህን ሕዝቦች ዘሮች እስከ ዛሬ ድረስ እንደሚደረገው የጕልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሰሎሞን መለመላቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች