ኃያል፥ ደግ፥ የሰው ልጆች ወዳጅ፥ ቆራጥ፥ አስተማማኝ፥ የማትሸበር፥ ሁሉን የምትችል፥ ሁሉን የምትቆጣጠር፥ አስተዋይ፥ ንጹሕ፥ ረቂቅ፥ የሆኑትን መንፈሶች ዘልቆ የሚገባ መንፈሳዊ አካል አላት።
ሰው ወዳጅ፥ የጥበብ ወዳጅዋ፥ ዐዋቂ፥ እውነተኛ፥ ግዳጅ የሌለበት፥ ትዕግሥተኛ፥ ሁሉን የሚችል፥ ሁሉንም የሚጐበኝ፥ ንጹሓትና አስተዋዮች፥ ረቂቃትም በሆኑ ነፍሳት የሚያድር ነው።