ልጁ እግሩን ሊታጠብ ወደ ወንዝ ወረደ፥ አንድ ትልቅ ዓሣም ከውሃው ውስጥ ዘሎ በመውጣት እግሩን ሊውጠው ተወረወረ፤ ልጁም ጮኸ።
መልአኩም፥ “ያን ዓሣ ያዘው” አለው፤ ያም ልጅ ዓሣውን ያዘው፤ ወደ የብስም አወጣው።