ማመዛዘን ይጠብቅሃል፥ ማስተዋልም ይከላከልልሃል፥
የመለየት ችሎታ ይጋርድሃል፤ ማስተዋልም ይጠብቅሃል።
አርቆ ማስተዋል ይጠብቅሃል፤ መገንዘብም ከክፉ ነገር ይከላከልልሃል።
መልካም ምክር ትጠብቅሃለች፤ የተቀደሰች ማስተዋልም ትጋርድሃለች።
አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና ፍጽምናና ቅንነት ይጠብቁኝ።
ብልሃትን ለአላዋቂዎች ለመስጠት ለወጣቶችም እውቀትንና ጥንቃቄን፥
አትተዋት፥ ትጠብቅሃለች፥ ውደዳት፥ ትንከባከብህማለች።
ብረት ቢደነዝዝ ሰውም ባይስለው ኃይልን ሊያበዛ ይገባዋል፥ ጥበብ ግን ሥራውን ለማከናወን ትጠቅመዋለች።
እንግዲህ ስለ አኗኗሯችሁ በጥንቃቄ ተጠበቁ፥ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው አይሁን፤