Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከክፉ መንገድ አንተን ለማዳን፥ ጠማማ ነገርን ከሚናገሩም ሰዎች፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ጥበብ ንግግራቸው ጠማማ ከሆነ ሰዎች፣ ከክፉዎችም መንገድ ታድንሃለች፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ጥበብ ከክፉ ሰዎች መንገድና ከጠማማ ንግግራቸው ያድንሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አንተን ከክፉ መንገድ፥ ምንም የሚታመን ነገርን ከማይናገር ሰውም ታድንህ ዘንድ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 2:12
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አትሳቱ፤ “መጥፎ ጓደኝነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።”


ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፥ የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።


ጌታን መፍራት ክፋትን መጥላት ነው፥ ትዕቢትንና እብሪትን ክፉንም መንገድ ጠማማውንም ንግግር እጠላለሁ።


ስለዚህም ጌታ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ፤ ርኩስንም አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፥


እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው ጠማማ ትምህርት በማስተማር ብዙ አማኞችን ወደ እነርሱ ይስባሉ።


አላዋቂነትን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በማስተዋልም መንገድ ሂዱ።”


ጠማማ ሁሉ በጌታ ፊት ርኩስ ነውና፥ ወዳጅነቱ ግን ከቅኖች ጋር ነው።


ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዓመፅን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለክፋት ምክንያት እንዳልሰጥ፥ ከድግሳቸውም አልቅመስ።


ጠማማ ልብም ከእኔ ይርቃል፥ ክፉን አላውቀውም።


ከንቱና ክፉ ሰው ጠማማ ንግግር ይዞ ይዞራል፥


የጻድቅ ከንፈሮች ደስ የሚያሰኝ ነገርን ያውቃሉ፥ የክፉዎች አፍ ግን ጠማማ ነገር ይናገራል።


ዐይኖችህ ልዩ ነገሮችን ያያሉ፥ ልብህም ጠማማ ነገርን ይናገራል።


በገዛ ልቡ የሚታመን ሰው ሞኝ ነው፥ በጥበብ የሚመላለስ ግን ይድናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች