ዮሐንስ 13:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ ስለሆንኩም መልካም ትናገራላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ፣ ‘መምህርና፣ ጌታ’ ትሉኛላችሁ፤ ትክክል ነው፤ እንደምትሉኝ እንዲሁ ነኝና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ‘መምህርና ጌታ’ ትሉኛላችሁ፤ እኔ መምህርና ጌታ ስለ ሆንኩ ያላችሁት ትክክል ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ‘መምህራችን፥ ጌታችንም’ ትሉኛላችሁ፤ መልካም ትላላችሁ፤ እኔ እንዲሁ ነኝና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ። |
ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር “ኢየሱስ የተረገመ ነው፤” የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር “ኢየሱስ ጌታ ነው፤” ሊል ማንም እንደማይችል አስታውቃችኋለሁ።
ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ እግዚአብሔር አብ አለን፤ እንዲሁም ነገር ሁሉ በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።
እናንተም ጌቶች ሆይ! ዛቻውን ትታችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ በእነርሱና በእናንተ ላይ የሚገዛው ጌታ በሰማይ እንዳለ ለሰው ፊትም እንደማያዳላ ታውቃላችሁ።
አዎን፤ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ ለማወቅ ስል ሁሉ ነገር ጉዳት እንደሆነ አድርጌ እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ነገሮች በማጣት ተጐዳሁ፤ እነርሱንም እንደ ጉድፍ አድርጌ ቈጠርኋቸው፤ በዚህም ክርስቶስን እንዳገኝ፥