Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማቴዎስ 20:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 የሰው ልጅም ሊያገለግል፥ ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 የሰው ልጅ እንዲያገለግሉት ሳይሆን፣ ለማገልገልና ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ለመስጠት መጥቷልና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 የሰው ልጅም ለማገልገልና ብዙዎችን ለማዳን ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት መጣ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማቴዎስ 20:28
35 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲሁም ክርስቶስ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ተሰውቷል። ለሁለተኛ ጊዜ ሲታይ ሊያድናቸው ለሚጠባበቁት ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን መዳንን ለማምጣት ነው።


ለመሆኑ ማነው ታላቅ? በማዕድ የተቀመጠ ወይስ የሚያገለግል? የተቀመጠው አይደለምን? እኔ ግን በእናንተ መሀል እንደሚያገለግል ነኝ።


መድኃኒታችንም ከኃጢአት ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኃጢአት መከራን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባችሁ በሥጋ ሞተ፥ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።


ራሱንም ለሁሉ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤ ይህም ምስክርነት ተገቢ በሆነው በራሱ ጊዜ የቀረበ ነበር፤


እንዲሁም ከታመነው ምስክር፥ ከሙታን በኩር ከሆነው፥ የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ፤ ለወደደን፥ ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥


የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ ታውቃላችሁ፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።


ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤


ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቁስል እናንተ ተፈውሳችኋል።


በእርሱም እንደ ጸጋው ባለጠግነት መጠን፥ በደሙ ቤዛነታችንን አገኘን፤ የበደላችንም ይቅርታ ሆነ።


ደግሞም እንዲህ አላቸው፤ “ይህ ስለ ብዙዎች የሚፈስስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው፤


ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የኪዳን ደሜ ይህ ነው።


ክርስቶስም እንዳፈቀራችሁ፥ ስለ እናንተም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ ያለው መባንና መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፥ በፍቅር ተመላለሱ።


ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ፥ ከሕግ እርግማን ዋጅቶናል፤ “በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው፤” ተብሎ ተጽፎአልና


ስለ ኃጢአታችን ለሞት ተላልፎ ተሰጠ፤ ለጽድቃችንም ተነሣ።


እርሱም የኃጢአታችን ማስተስረያ ነው፥ ለእኛ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።


ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ሲያመጣ፥ ሁሉ ነገር በእርሱና ለእርሱ የተፈጠረው፥ የመዳናቸውን ራስ በመከራ ይፈጽም ዘንድ ተገብቷልና።


አብም እንደሚያውቀኝ፥ እኔም አብን እንደማውቀው፤ ነፍሴንም ስለ በጎቼ አሳልፌ እሰጣለሁ።


በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?


እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፤ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን።


በኃይላቸው የሚታመኑ፥ በሀብታቸውም ብዛት የሚመኩ፥


ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጉድጓድ፥ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት የለውም፤” አለው።


እየራራለት፦ እሱን መታደጊያ ቤዛ አግኝቻለሁና ወደ መቃብር እንዳይወርድ አድነው ቢለው፥


ከእናንተም መካከል ፊተኛ መሆን የሚፈልግ የእናንተ ባርያ ይሁን፤


የሰው ልጅ ሊያገለግልና ሕይወቱን ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሊሰጥ መጣ እንጂ ሊገለገል አልመጣምና።”


ለሚቃጠልም መሥዋዕት አንድ ወይፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች